ማርቆስ 16:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም ሄዳ፣ ከርሱ ጋራ የነበሩት እያዘኑ ሲያለቅሱ አግኝታ ነገረቻቸው፤ እነርሱ ግን መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም ሄዳ፥ ከእርሱ ጋር የነበሩት እያዘኑ ሲያለቅሱ አግኝታ እርሱ ሕያው መሆኑንና ለእርሷም መታየቱን ነገረቻቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም ሄዳ፥ በሐዘንና በለቅሶ ላይ ለነበሩት ተከታዮቹ ነገረች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋ ሄዳ ከእርሱ ጋር ሆነው ለነበሩት ሲያዝኑና ሲያለቅሱ ሳሉ አወራችላቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋ ሄዳ ከእርሱ ጋር ሆነው ለነበሩት ሲያዝኑና ሲያለቅሱ ሳሉ አወራችላቸው፤ |
“በዚህ ጊዜ የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ላይ ይታያል፤ የምድር ወገኖች ሁሉ ያለቅሳሉ፤ የሰው ልጅም በሰማይ ደመና ሆኖ በኀይልና በታላቅ ክብር ሲመጣ ያዩታል፤
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “ሙሽራው ዐብሯቸው እያለ ዕድምተኞቹ እንዴት ሊያዝኑ ይችላሉ? ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል፤ በዚያም ጊዜ ይጾማሉ።
ወዲያውም ዶሮ ሁለተኛ ጮኸ። ጴጥሮስም፣ “ዶሮ ሁለት ጊዜ ከመጮኹ በፊት ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” ያለው የኢየሱስ ቃል ትዝ አለው። ከዚያም ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ።