ሉቃስ 8:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እየተጓዙ ሳሉም ኢየሱስ እንቅልፍ ወስዶት ተኛ፤ በዚህ ጊዜ በባሕሩ ላይ ማዕበል ተነሣ፤ ውሃውም ጀልባዋን ዘልቆ ስለ ገባ፣ አደጋ አፋፍ ላይ ደረሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እየሄዱም ሳሉ ኢየሱስ እንቅልፍ ወሰደው። ዓውሎ ነፋስም በሐይቁ ላይ ተነሣ፤ ውኃውም ታንኳይቱን ይሞላ ነበር፤ እነርሱም በአደጋ ላይ ስለ ነበሩ ተጨንቀው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በባሕሩ ላይ እየቀዘፉ ሲሄዱ ሳሉ ኢየሱስ አንቀላፋ፤ በዚያን ጊዜ ብርቱ ዐውሎ ነፋስ በባሕሩ ላይ ተነሣ፤ ውሃውም በጀልባው ውስጥ መሙላት ስለ ጀመረ አደጋው አስግቶአቸው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሲሄዱም አንቀላፋ፤ በባሕሩም ላይ ዐውሎ ነፋስ መጣ፤ ውኃዉም ታንኳቸውን ሞላው፤ እነርሱም ተጨነቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሲሄዱም አንቀላፋ። ዓውሎ ነፋስም በባሕር ላይ ወረደ፥ ውኃውም ታንኳይቱን ይሞላ ነበርና ይጨነቁ ነበር። |
“አንቺ የተጨነቅሽ ከተማ ሆይ፤ በዐውሎ ነፋስ የተናወጥሽ፣ ያልተጽናናሽም፤ እነሆ፤ በከበሩ ድንጋዮች አስጊጬ እገነባሻለሁ፤ በሰንፔር ድንጋይም እመሠርትሻለሁ።
ከዕለታቱ በአንድ ቀን፣ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ጀልባ ላይ ወጣ፤ ኢየሱስም፤ “ወደ ባሕሩ ማዶ እንሻገር” አላቸው፤ ከዚያም ጕዞ ቀጠሉ።
ከአድራሚጢስ ተነሥቶ በእስያ አውራጃ ባሕር ዳርቻ ላይ ወዳሉት ወደቦች በሚሄደው መርከብ ተሳፍረን የባሕር ጕዞ ጀመርን፤ በተሰሎንቄ ይኖር የነበረው የመቄዶንያ ሰው፣ አርስጥሮኮስም ከእኛ ጋራ ነበረ።
በድካማችን የማይራራልን ሊቀ ካህናት የለንምና፤ ነገር ግን እንደ እኛ በማንኛውም ነገር የተፈተነ ሊቀ ካህናት አለን፤ ይሁን እንጂ ምንም ኀጢአት አልሠራም።