የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፤ ስላንቺ ምን ማለት እችላለሁ? ከምንስ ጋራ አወዳድርሻለሁ? ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፤ አጽናናሽ ዘንድ፣ በምን ልመስልሽ እችላለሁ? ቍስልሽ እንደ ባሕር ጥልቅ ነው፤ ማንስ ሊፈውስሽ ይችላል?
ሉቃስ 7:31 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ በመቀጠል እንዲህ አለ፤ “እንግዲህ የዚህን ትውልድ ሰዎች በምን ልመስላቸው? ምንስ ይመስላሉ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም እንዲህ አለ፦ እንግዲህ የዚህን ትውልድ ሰዎች በምን እመስላቸዋለሁ? ማንንስ ይመስላሉ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “እንግዲህ ይህን ትውልድ በምን እመስለዋለሁ? ምንስ ይመስላል? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እንግዲህ የዚችን ትውልድ ሰዎች በምን እመስላቸዋለሁ? ማንንስ ይመስላሉ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ የዚችን ትውልድ ሰዎች በምን አስመስላቸዋለሁ? ማንንስ ይመስላሉ? |
የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፤ ስላንቺ ምን ማለት እችላለሁ? ከምንስ ጋራ አወዳድርሻለሁ? ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፤ አጽናናሽ ዘንድ፣ በምን ልመስልሽ እችላለሁ? ቍስልሽ እንደ ባሕር ጥልቅ ነው፤ ማንስ ሊፈውስሽ ይችላል?
በገበያ ቦታ ተቀምጠው እርስ በርሳቸው እየተጠራሩ እንዲህ የሚባባሉ ልጆችን ይመስላሉ፤ “ ‘ዋሽንት ነፋንላችሁ፤ አልጨፈራችሁም፤ ሙሾ አወረድንላችሁ፤ አላለቀሳችሁም።’