Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ማቴዎስ 7:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 “እንግዲህ ይህን ቃሌን ሰምቶ በተግባር የሚያውል፣ ቤቱን በዐለት ላይ የሠራን ብልኅ ሰው ይመስላል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 “ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዓለት ላይ የሠራ ጠቢብ ሰውን ይመስላል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 “ይህን ቃሌን ሰምቶ በሥራ ላይ የሚያውለው ሁሉ፥ ቤቱን በድንጋይ መሠረት ላይ የሠራ ብልኅ ሰውን ይመስላል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 “ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዐለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዓለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል።

Ver Capítulo Copiar




ማቴዎስ 7:24
41 Referencias Cruzadas  

እንግዲህ እነዚህን ነገሮች ዐውቃችሁ ብትፈጽሙ ትባረካላችሁ።


እርሱ ግን፣ “ብፁዓንስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚታዘዙት ናቸው” አለ።


ትእዛዞቹን ብንፈጽም እርሱን ማወቃችንን በዚህ ርግጠኞች እንሆናለን።


እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው፤ ትእዛዙንም የሚፈጽሙ ጥሩ ማስተዋል አላቸው፤ ምስጋናውም ለዘላለም ይኖራል።


በልቡ ጠቢብ የሆነ ትእዛዝ ይቀበላል፤ ለፍላፊ ቂል ግን ወደ ጥፋት ያመራል።


“ብትወድዱኝ ትእዛዜን ትጠብቃላችሁ።


የማዝዛችሁን ብትፈጽሙ ወዳጆቼ ናችሁ።


ከዚያም ሰውን፣ ‘እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፤ ከክፋትም መራቅ ማስተዋል ነው’ አለው።”


እኔ የአባቴን ትእዛዝ ጠብቄ በፍቅሩ እንደምኖር፣ እናንተም ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ።


በሰማይ ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፣ ወንድሜ፣ እኅቴና እናቴም ነው።”


ምስክርነትህን አሰላስላለሁና፣ ከአስተማሪዎቼ ሁሉ የላቀ አስተዋይ ልብ አገኘሁ።


የቃልህ ትርጓሜ ያበራል፤ አላዋቂዎችንም አስተዋዮች ያደርጋል።


የአስተዋዮች ጥበብ መንገዳቸውን ልብ ማለት ነው፤ የሞኞች ቂልነት ግን መታለል ነው።


ዐውሎ ነፋስ ሲነሣ ክፉዎች ተጠራርገው ይወሰዳሉ፤ ጻድቃን ግን ለዘላለም ጸንተው ይኖራሉ።


ክፉ ሰዎች ይገለበጣሉ፤ ድራሻቸውም ይጠፋል፤ የጻድቃን ቤት ግን ጸንቶ ይኖራል።


ዶፍ ወረደ፤ ጐርፍም ጐረፈ፤ ነፋስም ነፈሰ፤ ያን ቤት መታው፤ በዐለትም ላይ ስለ ተመሠረተ አልወደቀም።


ይህን ቃሌን ሰምቶ በተግባር የማያውለው ግን ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራን ሞኝ ሰው ይመስላል።


አንተ ጴጥሮስ ነህ፤ በዚህ ዐለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ የገሃነም ደጆችም አያሸንፏትም።


“በተገቢው ጊዜ ምግባቸውን እንዲሰጣቸው ባለቤቱ በቤተ ሰዎቹ ላይ የሾመው ታማኝና ብልኅ ባሪያ እንግዲህ ማነው?


ከእነርሱም ዐምስቱ ልጃገረዶች ዝንጉዎች፣ ዐምስቱ ደግሞ አስተዋዮች ነበሩ፤


አስተዋዮቹ ግን ከመብራታቸው ጋራ መጠባበቂያ ዘይት በማሰሮ ይዘው ነበር።


“አስተዋዮቹ ልጃገረዶች ግን መልሰው፣ ‘ያለን ዘይት ለእኛም ለእናንተም ላይበቃ ስለሚችል፣ ሄዳችሁ ከሻጮች ለራሳችሁ ግዙ’ አሏቸው።


ምክንያቱም በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን የሚባሉት ለሕጉ የሚታዘዙ እንጂ፣ ሕጉን የሚሰሙ አይደሉም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios