በዚያም ሰዎች አንድ ሽባ ሰው በቃሬዛ ተሸክመው ወደ እርሱ አመጡ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን፣ “አይዞህ አንተ ልጅ፤ ኀጢአትህ ተሰርዮልሃል” አለው።
ሉቃስ 5:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘ኀጢአትህ ተሰረየልህ’ ከማለትና ‘ተነሥተህ ሂድ’ ከማለት የትኛው ይቀልላል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘ኀጢአቶችህ ተሰረዩልህ፤’ ከማለትና ‘ተነሣና ሂድ፤’ ከማለት የትኛው ይቀላል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለመሆኑ ‘ኃጢአትህ ይቅር ተብሎልሃል፥’ ከማለትና ‘ተነሥተህ ሂድ!’ ከማለት የትኛው ይቀላል? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀጢአትህ ተሰረየልህ ከማለትና ተነሥተህ ሂድ ከማለት ማናቸው ይቀላል? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኃጢአትህ ተሰረየችልህ ከማለት ወይስ፦ ተነሣና ሂድ ከማለት ማናቸው ይቀላል? |
በዚያም ሰዎች አንድ ሽባ ሰው በቃሬዛ ተሸክመው ወደ እርሱ አመጡ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን፣ “አይዞህ አንተ ልጅ፤ ኀጢአትህ ተሰርዮልሃል” አለው።
ነገር ግን ይህን ያልሁት የሰው ልጅ በምድር ላይ ኀጢአትን ለማስተስረይ ሥልጣን እንዳለው ታውቁ ዘንድ ነው።” ከዚያም ሽባውን ሰው፣ “ተነሥተህ ዐልጋህን ተሸክመህ ወደ ቤትህ ሂድ እልሃለሁ” አለው።