ሉቃስ 4:37 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእርሱም ዝና በአካባቢው ወዳለው ስፍራ ሁሉ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ እርሱም የተነገረው በዙሪያው ባለው አገር፥ በሁሉ ስፍራ ተሰራጭቶ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኢየሱስም ዝና በዚያ አገር ዙሪያ ሁሉ ተሰማ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዝናውም በዙሪያዉ ባሉ መንደሮች ሁሉ ወጣ፤ ተሰማም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዝናም በዙሪያው ባለች አገር ወደ ስፍራው ሁሉ ስለ እርሱ ወጣ። |
ሰውየው ግን በሄደበት ሁሉ ነገሩን በሰፊው አወራ፤ ወሬውንም አሠራጨ። በዚህ ምክንያት ኢየሱስ ወደ ማንኛውም ከተማ በግልጽ መግባት አልተቻለውም፤ ከዚህም የተነሣ ከከተማ ውጭ በሚገኙ ምድረ በዳዎች መኖር ጀመረ፤ ሰዎች ግን ከየአቅጣጫው እርሱ ወዳለበት መምጣት አላቋረጡም።
የኢየሱስ ስም እየታወቀ በመምጣቱ፣ ንጉሥ ሄሮድስ ይህንኑ ሰማ። አንዳንዶችም፣ “የዚህ ዐይነት ታምር በርሱ የሚሠራው መጥምቁ ዮሐንስ ከሙታን ቢነሣ ነው” ይሉ ነበር።