እያዘገሙም ሲነጋገሩ ሳለ፣ የእሳት ሠረገላና የእሳት ፈረሶች ድንገት በመካከላቸው ገብተው ሁለቱን ለዩአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ዐረገ።
ሉቃስ 24:51 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እየባረካቸውም ሳለ፣ ከእነርሱ ተለይቶ ወደ ሰማይ ዐረገ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እየባረካቸውም ከእነርሱ ተለየ፤ ወደ ሰማይም ዐረገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሲባርካቸውም ሳለ ከእነርሱ ተለይቶ ወደ ሰማይ ዐረገ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እየባረካቸውም ራቃቸው፤ ወደ ሰማይም ዐረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ። |
እያዘገሙም ሲነጋገሩ ሳለ፣ የእሳት ሠረገላና የእሳት ፈረሶች ድንገት በመካከላቸው ገብተው ሁለቱን ለዩአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ዐረገ።
ኢየሱስም፣ “ገና ወደ አብ ስላላረግሁ፣ አትንኪኝ፤ ይልቁንስ ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ፣ ‘ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ፣ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዐርጋለሁ’ ብሏል ብለሽ ንገሪአቸው” አላት።
እርሱ የእግዚአብሔር ክብር ነጸብራቅና የባሕርዩ ትክክለኛ ምሳሌ ሆኖ፣ በኀያል ቃሉ ሁሉን ደግፎ ይዟል። የኀጢአት መንጻት ካስገኘ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ።