La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 23:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሄሮድስም ኢየሱስን ብዙ ጊዜ ሊያየው ይፈልግ ስለ ነበር፣ ባየው ጊዜ እጅግ ደስ አለው፤ ስለ እርሱ ሰምቶ ስለ ነበር፣ ታምራት ሲሠራ ለማየት ተስፋ ያደርግ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሄሮድስም ኢየሱስን ባየው ጊዜ እጅግ ደስ አለው፤ ስለ እርሱ ስለ ሰማ ከብዙ ጊዜ ጀምሮ ሊያየው ይመኝ ነበርና፤ ተአምር ሲሠራ ሊያይ ተስፋ ያደርግ ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሄሮድስ ኢየሱስን ባየ ጊዜ እጅግ ደስ አለው፤ ስለ ኢየሱስ ይሰማ ነበርና ሊያየው ብዙ ጊዜ ይመኝ ነበር፤ እንዲሁም ኢየሱስ ተአምር ሲያደርግ ለማየት ተስፋ ያደርግ ነበር።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሄሮ​ድ​ስም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ባየው ጊዜ እጅግ ደስ አለው፤ ዜና​ውን ስለ​ሚ​ሰማ ከረ​ጅም ጊዜ ጀምሮ ሊያ​የው ይሻ ነበ​ርና፤ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ው​ንም ተአ​ም​ራት ሊያይ ይመኝ ነበ​ርና።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሄሮድስም ኢየሱስን ባየው ጊዜ እጅግ ደስ አለው፤ ስለ እርሱ ስለ ሰማ ከብዙ ጊዜ ጀምሮ ሊያየው ይመኝ ነበርና፥ ምልክትም ሲያደርግ ሊያይ ተስፋ ያደርግ ነበር።

Ver Capítulo



ሉቃስ 23:8
8 Referencias Cruzadas  

ንዕማን ግን ተቈጥቶ እንዲህ በማለት ሄደ፤ “እኔ እኮ በርግጥ ወደ እኔ መጥቶ በመቆም የአምላኩን የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ፣ በእጁም ዳስሶ ከለምጽ በሽታዬ የሚፈውሰኝ መስሎኝ ነበር።


በዚያ ጊዜ የአራተኛው ክፍል ገዥ የነበረው፣ ሄሮድስ ስለ ኢየሱስ ሰማ፤


የኢየሱስ ስም እየታወቀ በመምጣቱ፣ ንጉሥ ሄሮድስ ይህንኑ ሰማ። አንዳንዶችም፣ “የዚህ ዐይነት ታምር በርሱ የሚሠራው መጥምቁ ዮሐንስ ከሙታን ቢነሣ ነው” ይሉ ነበር።


ከዚህ በኋላ፣ ሕዝቡን ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ወደ እርሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ሊከተለኝ የሚወድድ ቢኖር ራሱን ይካድ፤ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።


እርሱም፣ “ ‘ባለመድኀኒት ሆይ፤ ራስህን ፈውስ፤ በቅፍርናሆም ስታደርግ የሰማነውን ነገር እዚህ በራስህ ከተማ ደግሞ አድርግ’ የሚለውን ምሳሌ እንደምትጠቅሱብኝ ጥርጥር የለውም” አላቸው።


“እጄን የምጭንበት ሰው ሁሉ መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበል ይህን ሥልጣን ለእኔም ስጡኝ።”