እግዚአብሔር ምድርን ለማናወጥ በሚነሣበት ጊዜ፣ ሰዎች ከአስፈሪነቱ ከግርማውም የተነሣ፣ ወደ ዐለት ዋሻ፣ ወደ መሬትም ጕድጓድ ለመሸሸግ ይሮጣሉ።
ሉቃስ 23:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ፣ “ ‘ተራሮችን፣ “ውደቁብን!” ኰረብቶችንም፣ “ሸፍኑን!” ’ ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ ተራራዎችን ‘በላያችን ውደቁ፤’ ኮረብቶችንም ‘ሰውሩን፤’ ማለት ይጀምራሉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ ሰዎች ተራራዎችን፥ ‘በላያችን ውደቁ!’ ኮረብቶችንም፥ ‘ሸሽጉን!’ ማለት ይጀምራሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያንጊዜም ተራሮችን ‘በላያችን ውደቁ፤ ኮረብቶችንም ሰውሩን’ ይሉአቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜ ተራራዎችን፦ በላያችን ውደቁ፥ ኮረብቶችንም፦ ሰውሩን ይሉ ዘንድ ይጀምራሉ፤ |
እግዚአብሔር ምድርን ለማናወጥ በሚነሣበት ጊዜ፣ ሰዎች ከአስፈሪነቱ ከግርማውም የተነሣ፣ ወደ ዐለት ዋሻ፣ ወደ መሬትም ጕድጓድ ለመሸሸግ ይሮጣሉ።
የእስራኤል ኀጢአት የሆነው፣ የአዌን ማምለኪያ ኰረብታ ይጠፋል፤ እሾኽና አሜከላ ይበቅልባቸዋል፤ መሠዊያዎቻቸውንም ይወርሳል፤ በዚያ ጊዜ ተራሮችን፣ “ውደቁብን!” ኰረብቶችንም፣ “ሸፍኑን!” ይላሉ።