ሉቃስ 23:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡም ሁሉ በአንድ ላይ፣ “ይህን ሰው ወዲያ አስወግደው! በርባንን ፍታልን!” እያሉ ጮኹ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁሉም በአንድነት “ይህን አስወግደው፤ በርባንንም ፍታልን፤” እያሉ ጮኹ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሕዝቡ ሁሉ “ይህን ሰው አስወግደው! በርባንን ግን ፍታልን!” እያሉ በአንድ ድምፅ ጮኹ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁሉም በሙሉ፥ “ይህን አስወግደው፥ ስቀለውም፥ በርባንን ግን ፍታልን” ብለው ጮሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁላቸውም በአንድነት፦ ይህን አስወግድ፥ በርባንንም ፍታልን እያሉ ጮኹ፤ |
ሕዝቡም ይህን ቃል እስኪናገር ድረስ ሰሙት፤ ከዚህ በኋላ ግን ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ፣ “ይህስ ከምድር ገጽ ይወገድ! በሕይወት መኖር አይገባውም!” ብለው ጮኹበት።