ሉቃስ 21:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምድሪቱ ላይ ታላቅ መከራ ይሆናል፤ በዚህም ሕዝብ ላይ ቍጣ ይመጣል፤ ስለዚህ በዚያ ወቅት ለነፍሰ ጡሮችና ለሚያጠቡ እናቶች ወዮላቸው! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በነዚያ ቀናት ለነፍሰ ጡሮችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው፤ ታላቅ ችግር በምድር ላይ፥ በዚህም ሕዝብ ላይ ቁጣ ይሆናልና፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ ለነፍሰጡሮችና ለሚያጠቡ እመጫቶች ወዮላቸው! በምድር ላይ ታላቅ መከራ ይሆናል፤ በዚህም ሕዝብ ላይ የእግዚአብሔር ቊጣ ይመጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን በዚያ ወራት ለፀነሱና ለሚያጠቡ ወዮላቸው፤ በምድር ላይ ጽኑ መከራ፥ በዚህም ሕዝብ ላይ መቅሠፍት ይሆናልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ወራት ለእርጕዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው፤ ታላቅ ችግር በምድር ላይ፥ በዚህም ሕዝብ ላይ ቍጣ ይሆናልና፤ |
እነርሱም፣ “እነዚህ ሕፃናት የሚሉትን ትሰማለህ?” አሉት። ኢየሱስም፣ “አዎን እሰማለሁ፤ እንዲህ የሚለውን ከቶ አላነበባችሁምን? “ ‘ከልጆችና ጡት ከሚጠቡ፣ ሕፃናት አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ።’ ”
እነርሱም፣ “እነዚያን ክፉዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሎ ከወይኑ ዕርሻ ተገቢውን ፍሬ በወቅቱ ለሚያስረክቡት ለሌሎች ገበሬዎች ያከራያል” አሉት።
ይኸውም ይድኑ ዘንድ ለአሕዛብ እንዳንናገር ለመከልከል ነው፤ በዚህ ሁኔታ ኀጢአታቸውን ሁልጊዜ በራሳቸው ላይ እስከ መጨረሻው እያከማቹ ይሄዳሉ። ቍጣውም በእነርሱ ላይ ያለ ልክ መጥቷል።
ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት የሚጀምርበት ጊዜ ደርሷልና፤ እንግዲህ ፍርድ የሚጀምረው በእኛ ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ ሰዎች መጨረሻቸው ምን ይሆን?