ሉቃስ 14:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁለታችሁንም የጋበዘው መጥቶ፣ ስፍራውን ‘ለዚህ ሰው ልቀቅለት’ ይልሃል፤ አንተም እያፈርህ ወደ ዝቅተኛው ስፍራ ትሄዳለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘ለዚህ ሰው ስፍራ ተውለት’ ይልሃል፤ በዚያን ጊዜም እያፈርህ ዝቅተኛውን ስፍራ መያዝ ትጀምራለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ፥ ሁለታችሁንም የጋበዛችሁ ሰው ወደ አንተ መጥቶ፦ ‘ይህን ስፍራ ለዚህ ሰው ልቀቅለት’ ይልሃል፤ ያን ጊዜ በታላቅ ኀፍረት ወደ ዝቅተኛው ቦታ ወርደህ ትቀመጣለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኋላ ያ አንተንም እርሱንም የጠራ መጥቶ፦ ይህን ቦታ ለእርሱ ተውለት ይልሃልና፤ ያንጊዜም አፍረህ ትመለሳለህ፤ ወደ ዝቅተኛ ቦታም ትወርዳለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለዚህ ስፍራ ተውለት ይልሃል፥ በዚያን ጊዜም እያፈርህ በዝቅተኛው ስፍራ ልትሆን ትጀምራለህ። |
እንግዲህ ለንስሓ የሚገባ ፍሬ አፍሩ፤ ደግሞም በልባችሁ፣ ‘አብርሃም አባት አለን’ ማለትን አትጀምሩ፤ እግዚአብሔር ከእነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ማስነሣት እንደሚችል እነግራችኋለሁና።