ሉቃስ 13:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታም መልሶ እንዲህ አለው፤ “እናንተ ግብዞች፤ ከእናንተ መካከል አንድ ሰው በሬውን ወይም አህያውን በሰንበት ቀን ከማደሪያው ፈትቶ ውሃ ሊያጠጣ ይወስደው የለምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም መልሶ እናንተ ግብዞች! ከእናንተ እያንዳንዱ በሰንበት በሬውን ወይስ አህያውን ከግርግሙ ፈትቶ ውሃ ሊያጠጣው ይወስደው የለምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታ ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “እናንተ ግብዞች፥ ከእናንተስ እያንዳንዱ በሰንበት ቀን በሬውን ከተዘጋበት አውጥቶ፥ ወይም አህያውን ከታሰረበት ፈቶ ውሃ ወደሚያጠጣበት ቦታ ይወስደው የለምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስም መልሶ አላቸው፥ “እናንት ግብዞች፥ እናንተሳ አህያችሁን ወይም በሬአችሁን በሰንበት ቀን ገለባ ከሚበላበት አትፈቱትምን? ውኃ ልታጠጡትስ አትወስዱትምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታም መልሶ፦ እናንተ ግብዞች፥ ከእናንተ እያንዳንዱ በሰንበት በሬውን ወይስ አህያውን ከግርግሙ ፈትቶ ውኃ ሊያጠጣው ይወስደው የለምን? |
“እናንተ ግብዞች የኦሪት ሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! ሰዎች ወደ መንግሥተ ሰማይ እንዳይገቡ በሩን ስለምትዘጉባቸው እናንተ ራሳችሁ አትገቡም፤ መግባት የሚፈልጉትንም አታስገቡም። [
በዚያ ጊዜ፣ በብዙ ሺሕ የሚቈጠር ሕዝብ እርስ በርስ እስኪረጋገጥ ድረስ ተሰብስቦ ሳለ፣ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ይል ጀመር፤ “ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠንቀቁ፤ ይህም ግብዝነት ነው።
በራስህ ዐይን ውስጥ ያለውን ግንድ ሳታይ ወንድምህን፣ ‘ወንድሜ ሆይ፤ በዐይንህ ውስጥ ያለውን ጕድፍ ላውጣልህ’ እንዴት ልትለው ትችላለህ? አንተ ግብዝ፤ አስቀድመህ በዐይንህ ውስጥ ያለውን ግንድ አውጣ፤ ከዚያም በወንድምህ ዐይን ውስጥ ያለውን ጕድፍ ለማውጣት አጥርተህ ታያለህ።