Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ምሳሌ 11:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ክፉ ሰው ባልንጀራውን በአፉ ያጠፋል፤ ጻድቃን ግን በዕውቀት ያመልጣሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እኩይ ሰው በአፉ ባልንጀራውን ያጠፋል፥ ጻድቃን ግን በእውቀት ይድናሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እግዚአብሔርን የማያመልኩ በንግግራቸው ሰውን ያጠፋሉ፤ ጻድቃን ግን በዕውቀት ይድናሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 በክፉዎች አፍ የሀገር ወጥመድ አለ፥ የጻድቃን ዕውቀት ግን መልካም ጎዳና ናት።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 11:9
26 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ አራት መቶ ነቢያትን በአንድነት ሰብስቦ፣ “በገለዓድ በምትገኘው ራሞት ላይ ልዝመት ወይስ ልቅር?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም፣ “እግዚአብሔር በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታልና ዝመትባት” አሉት።


ይህም የሆነው ዐመፀኛው ሰው ሕዝቡን እንዳይገዛ፣ ወጥመድም በፊታቸው እንዳይዘረጋ ነው።


እግዚአብሔርን የሚረሱ መጨረሻቸው እንዲህ ነው፤ አምላክ የለሽ ኑሮ የሚኖሩም ሁሉ ተስፋቸው ትጠፋለች።


የሚዘልፈኝ ጠላት አይደለምና፤ ቢሆንማ ኖሮ በታገሥሁት ነበር፤ የሚጠላኝ፣ ራሱንም ቀና ቀና ያደረገብኝ ባላንጣ አይደለም፤ ቢሆንማ ከርሱ በተሸሸግሁ ነበር።


ቅኖችን ጽድቃቸው ትታደጋቸዋለች፤ ወስላቶች ግን በክፉ ምኞታቸው ይጠመዳሉ።


ጻድቅ ከመከራ ይድናል፤ ይልቁን መከራው በክፉው ላይ ይደርሳል።


ክፉ ሰው ባልንጀራውን ያባብለዋል፤ መልካም ወዳልሆነውም መንገድ ይመራዋል።


“በውስጣቸው ነጣቂ ተኵላዎች ሆነው ሳሉ የበግ ለምድ ለብሰው መካከላችሁ በመግባት ከሚያሸምቁ ሐሰተኛ ነቢያት ተጠንቀቁ።


“ ‘የጥፋት ርኩሰት’ ስፍራው ባልሆነ ቦታ ቆሞ በምታዩት ጊዜ አንባቢው ያስተውል፤ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፤


ከእናንተው መካከል እንኳ የራሳቸውን ደቀ መዛሙርት ለማፍራት እውነትን የሚያጣምሙ ይነሣሉ።


ለእናንተ የምጽፍላችሁ እውነቱን ስለማታውቁት አይደለም፤ ነገር ግን ስለምታውቁት እና ምንም ውሸት ከእውነቱ ስላልሆነ ነው።


እናንተ ግን ከርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በውስጣችሁ ይኖራልና ማንም እንዲያስተምራችሁ አያስፈልግም፤ ነገር ግን የርሱ ቅባት ስለ ሁሉም ነገር፣ እውነተኛ የሆነውን እና ሐሰት ያልሆነው እናንተን እንደሚያስተምር፣ እናንተንም እንዳስተማራችሁ በርሱ ኑሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos