ሉቃስ 12:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የማይገለጥ የተሸፈነ፣ የማይታወቅ የተሰወረ ምንም የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለምና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተሸፈነ ነገር ሳይገለጥ አይቀርም፤ የተሰወረውም ሳይታወቅ አይቀርም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የማይገለጥ የተሰወረ፥ የማይታይም የተሸሸገ የለምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለም። |
ለእኔ የሚገባውን መሥዋዕት ያቀርባሉ፤ ሥጋውንም ይበላሉ፤ እግዚአብሔር ግን በእነርሱ አልተደሰተም፤ ስለዚህ ክፋታቸውን ያስታውሳል፤ ኀጢአታቸውን ይቀጣል፤ ወደ ግብጽም ይመለሳሉ።
ስለዚህ ጊዜው ሳይደርስ በምንም ነገር አትፍረዱ፤ ጌታ እስኪመጣ ጠብቁ። እርሱ በጨለማ ውስጥ የተሰወረውን ወደ ብርሃን ያመጣዋል፤ በሰዎች ልብ ውስጥ ያለውንም ሐሳብ ይገልጠዋል። በዚያ ጊዜ እያንዳንዱ ሰው የሚገባውን ምስጋና ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል።