ሉቃስ 1:47 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም መንፈሴም በመድኀኒቴ በእግዚአብሔር ደስ ትሠኛለች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ትደሰታለች፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልቡናዬም በአምላኬ በመድኀኒቴ ሐሤት ታደርጋለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤ |
አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፤ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፤ እልል በዪ፤ እነሆ፤ ጻድቁና አዳኙ ንጉሥሽ፣ ትሑት ሆኖ፣ በአህያ ላይ ተቀምጦ፣ በአህያ ግልገል፣ በውርንጫዪቱ ላይ ሆኖ ወደ አንቺ ይመጣል።
እርሱ ብቻ አዳኛችን ለሆነው አምላክ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከዘመናት ሁሉ በፊት፣ አሁንና እስከ ዘላለምም ድረስ ክብር፣ ግርማ፣ ኀይልና ሥልጣን ይሁን! አሜን።