“ካህናት ሆነው ያገለግሉኝ ዘንድ ከእስራኤላውያን መካከል ወንድምህ አሮንን ከወንዶች ልጆቹ ከናዳብ፣ ከአብዩድ፣ ከአልዓዛርና ከኢታምር ጋራ ወደ አንተ አቅርባቸው።
ዘሌዋውያን 8:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አሮንንና ልጆቹን፣ ልብሰ ተክህኖውን፣ የመቅቢያ ዘይቱን፣ ለኀጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን ወይፈን፣ ሁለቱን አውራ በጎችና ቂጣ ያለበትን መሶብ አምጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አሮንን፥ ከእርሱም ጋር ልጆቹን፥ ልብሱንም፥ የቅባቱንም ዘይት፥ ለኃጢአት መሥዋዕትም የሚቀርበውን ወይፈን፥ ሁለቱንም አውራ በጎች፥ እርሾ ያልነካው ቂጣ የሚቀመጥበትንም መሶብ ውሰድ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አሮንንና ወንዶች ልጆቹን እንዲሁም የክህነት ልብሱን፥ የቅባቱን ዘይት፥ ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚቀርበውን ኰርማ ሁለቱን የበግ አውራዎች፥ እርሾ ያልነካው ቂጣ ያለበትን መሶብ፥ አብረህ አምጣ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አሮንን፥ ከእርሱም ጋር ልጆቹን፥ ልብሱንም፥ የቅብዐቱንም ዘይት፥ ለኀጢአት መሥዋዕትም የሆነውን ወይፈን፥ ሁለቱንም አውራ በጎች፥ የቂጣውንም እንጀራ መሶብ ውሰድ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሮንን፥ ከእርሱም ጋር ልጆቹን፥ ልብሱንም፥ የቅብዓቱንም ዘይት፥ ለኃጢአት መሥዋዕትም የሆነውን ወይፈን፥ ሁለቱንም አውራ በጎች፥ የቂጣውንም እንጀራ ሌማት ውሰድ፤ |
“ካህናት ሆነው ያገለግሉኝ ዘንድ ከእስራኤላውያን መካከል ወንድምህ አሮንን ከወንዶች ልጆቹ ከናዳብ፣ ከአብዩድ፣ ከአልዓዛርና ከኢታምር ጋራ ወደ አንተ አቅርባቸው።
በመቅደሱ ሲያገለግሉ የሚለበሱት የተፈተሉት ቀሚሶች፣ ለካህኑ ለአሮን የተቀደሱት ቀሚሶችና ወንዶች ልጆቹ ካህናት ሆነው ሲያገለግሉ የሚያደርጓቸው ቀሚሶች ናቸው።
ካህኑም ከበፍታ የተሠራ የውስጥ ሱሪውን ካጠለቀ በኋላ፣ የበፍታ ቀሚሱን ይልበስ፤ እሳቱ በመሠዊያው ላይ መሥዋዕቱን ከበላው በኋላ የሚቀረውን ዐመድ አንሥቶ፣ በመሠዊያው አጠገብ ያፍስስ።
እርሱም እንደ ሌሎቹ ሊቃነ ካህናት መጀመሪያ ስለ ራሱ ኀጢአት፣ ከዚያም ስለ ሕዝቡ ኀጢአት በየቀኑ መሥዋዕት ማቅረብ አያስፈልገውም፤ ራሱን በሰጠ ጊዜ፣ ስለ ኀጢአታቸው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መሥዋዕት አቅርቧልና።