ዘሌዋውያን 7:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሥቡን በሙሉ ያቅርብ፤ ይኸውም፦ ላቱን፣ የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሥብ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስቡንም ሁሉ፥ ላቱንም፥ የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ ያቀርበዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስቡ ሁሉ ተገፎ፥ ይኸውም የላቱ ስብ፥ የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነው ስብ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስቡንም ሁሉ፥ ላቱንም፥ የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ ሁሉ፥ በአንጀቱም ላይ ያለውን ስብ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስቡንም ሁሉ፥ ላቱንም፥ የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ ያቀርበዋል። |
ከዚያም በሆድ ዕቃዎች ያለውን ስብ ሁሉ፣ የጕበቱን መሸፈኛና ሁለቱንም ኵላሊቶች በዙሪያቸው ካለው ስብ ጋራ ወስደህ በመሠዊያው ላይ አቃጥላቸው።