በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከመጋረጃው በስተውጭ ይኸውም ከምስክሩ ታቦት ፊት ለፊት፣ አሮንና ወንድ ልጆቹ መብራቶቹን ከምሽት እስከ ንጋት በእግዚአብሔር ፊት እንዲበሩ ያድርጉ፤ ይህም በእስራኤላውያን ዘንድ ከትውልድ እስከ ትውልድ የዘላለም ሥርዐት ይሆናል።
ዘሌዋውያን 24:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሮንም በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከምስክሩ ታቦት መጋረጃ ውጭ በእግዚአብሔር ፊት ያሉትን መብራቶች ከምሽት እስከ ንጋት ያለ ማቋረጥ ያሰናዳቸው፤ ይህም ከትውልድ እስከ ትውልድ ሥርዐት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሮን ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከምስክሩ መጋረጃ ውጭ በጌታ ፊት ሁልጊዜ ያዘጋጀው፤ ለዘለዓለም ለልጅ ልጃችሁ ሥርዓት ይሁን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሮን በየምሽቱ መብራቱን ያቀጣጥላል፤ እርሱም በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ባለው በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ለፊት ካለው መጋረጃ ውጪ በእግዚአብሔር ፊት እስከ ንጋት ድረስ ሲበራ ያድራል፤ ይህም ድንጋጌ በሚመጡት ዘመናት ሁሉ ተጠብቆ ይኖራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምስክሩ ድንኳን ከመጋረጃው ውጭ አሮንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት ሁል ጊዜ ያበሩታል፤ ለዘለዓለም ለልጅ ልጃችሁ ሥርዐት ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምስክሩ መጋረጃ ውጭ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አሮን ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት ሁልጊዜ ያሰናዳው፤ ለዘላለም ለልጅ ልጃችሁ ሥርዓት ይሁን። |
በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከመጋረጃው በስተውጭ ይኸውም ከምስክሩ ታቦት ፊት ለፊት፣ አሮንና ወንድ ልጆቹ መብራቶቹን ከምሽት እስከ ንጋት በእግዚአብሔር ፊት እንዲበሩ ያድርጉ፤ ይህም በእስራኤላውያን ዘንድ ከትውልድ እስከ ትውልድ የዘላለም ሥርዐት ይሆናል።
ሳሙኤልም ደግሞ የእግዚአብሔር ታቦት ባለበት፣ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ተኝቶ ነበር፤ የእግዚአብሔር መብራትም ገና አልጠፋም ነበር።