ዘሌዋውያን 18:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኖራችሁበት በግብጽ እነርሱ እንደሚያደርጉት አታድርጉ፤ እኔ በማስገባችሁ በከነዓን እንደሚያደርጉትም አታድርጉ፤ ልማዳቸውንም አትከተሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተቀመጣችሁባት በግብጽ ምድር እንደሚያደርጉት እናንተም እንዲሁ አታድርጉ፤ እኔም ወደማመጣችሁ ስፍራ ወደ ሆነው በከነዓን ምድር ላይ እንደሚያደርጉት እናንተም እንዲሁ አታድርጉ፤ በሥርዓታቸውም አትሂዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በኖራችሁባት በግብጽ ምድር፥ ወይም አሁን እኔ በማስገባችሁ በከነዓን ምድር የሚኖሩ አሕዛብ የሚያደርጉትን አታድርጉ፤ ሥርዓታቸውንም አትከተሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ተቀመጣችሁባት እንደ ግብፅ ምድር ሥራ አትሥሩ፤ እኔም ወደ እርስዋ እንደማገባችሁ እንደ ከነዓን ምድር ሥራ አትሥሩ፤ በሥርዐታቸውም አትሂዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ተቀመጣችሁባት እንደ ግብፅ ምድር ሥራ አትሥሩ፤ እኔም ወደ እርስዋ እንደማገባችሁ እንደ ከነዓን ምድር ሥራ አትሥሩ፤ በሥርዓታቸውም አትሂዱ። |
በግብጽ የጀመረችውን አመንዝራነቷን አልተወችም፤ በዚያ ወንዶች በወጣትነቷ ከርሷ ጋራ ተኙ፤ የድንግልናዋን ጡት አሻሹ፤ ፍትወታቸውን አፈሰሱባት።
መልካም፣ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በአእምሯችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።
አምላክህ እግዚአብሔር እነርሱን ከፊትህ ካስወጣቸው በኋላ በልብህ፣ “ይህችን ምድር እንድወርስ እግዚአብሔር ወደዚህ ያመጣኝ፣ ከጽድቄ የተነሣ ነው” አትበል። በዚህ አይደለም፤ እነዚህን አሕዛብ እግዚአብሔር ከፊትህ የሚያሳድዳቸው በክፋታቸው ምክንያት ነው።