ዘሌዋውያን 17:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔር ማደሪያ ፊት ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጎ ለማቅረብ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ባያመጣው፣ ያ ሰው በከንቱ ደም እንዳፈሰሰ ይቈጠራል፤ ደም በማፍሰሱም ከወገኖቹ ተለይቶ ይጥፋ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታ ማደሪያ ፊት ለፊት ለጌታ እንደ ቁርባን አድርጎ ለማቅረብ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ባያመጣው፥ ደሙ በዚያ ሰው ላይ ይቈጠርበታል፤ ደም አፍስሶአል፤ ያም ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጥፋ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተቀደሰው ስፍራ ለእግዚአብሔር ቊርባን ያቀርብ ዘንድ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ባያመጣው፥ ደም በከንቱ እንዳፈሰሰ ተቈጥሮ ይፈረድበታል፤ ከሕዝቡም ይለያል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ያለው የተመረጠ የሚቃጠል መሥዋዕት፥ ወይም የድኅነት መሥዋዕት ያደርገው ዘንድ ወደ ምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ባያመጣው፥ በሌላም ቦታ ቢያርደው፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ፊት ለእግዚአብሔር ቍርባን ያቀርብ ዘንድ ወደ ምስክሩ ድንኳን ባያመጣው፥ ደሙ በዚያ ሰው ላይ ይቈጠርበታል፤ ደም አፍስሶአልና፤ ያም ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእግዚአብሔር ማደሪያ ፊት ለእግዚአብሔር ቍርባን ያቀርብ ዘንድ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ባያመጣው፥ ደሙ በዚያ ሰው ላይ ይቈጠርበታል፤ ደም አፍስሶአል፤ ያም ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ። |
ለሰባት ቀናት እርሾ የሌለበት ቂጣ ብሉ። በመጀመሪያው ቀን እርሾን ሁሉ ከቤታችሁ አስወግዱ፤ በእነዚህ ሰባት ቀናት እርሾ ያለበትን ቂጣ የበላ ማንኛውም ሰው ከእስራኤል ይወገድ።
ነገር ግን ወይፈን የሚሠዋልኝ፣ ሰው እንደሚገድል ነው፤ የበግ ጠቦት የሚያቀርብልኝ፣ የውሻ ዐንገት እንደሚሰብር ሰው ነው፤ የእህል ቍርባን የሚያዘጋጅልኝ፣ የዕሪያ ደም እንደሚያቀርብልኝ ሰው ነው፤ የመታሰቢያን ዕጣን የሚያጥንልኝም፣ ጣዖትን እንደሚያመልክ ሰው ነው፤ የገዛ መንገዳቸውን መርጠዋል፤ ነፍሳቸውም በርኩሰታቸው ደስ ይላታል።
በቅዱሱ ተራራዬ፣ ከፍ ባለው የእስራኤል ተራራ ላይ በዚያ ምድር የእስራኤል ቤት ሁሉ ያመልከኛልና፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ እኔም በዚያ እቀበላቸዋለሁ። ቍርባናችሁንና በኵራታችሁን ከተቀደሱ መሥዋዕቶቻችሁ ሁሉ ጋራ በዚያ እሻለሁ።
“ ‘መባው በሚቃጠል መሥዋዕትነት ከላሞች መንጋ መካከል የሚቀርብ ከሆነ፣ ነቀፋ የሌለበትን ተባዕቱን መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ያቅርበው።
“ ‘ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በመካከላቸው የሚኖር ማንኛውም መጻተኛ ደም ቢበላ፣ ደም በሚበላው በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከብድበታለሁ፤ ከወገኖቹም ለይቼ አጠፋዋለሁ፤
የማንኛውም ፍጡር ሕይወት ደሙ ነውና። ስለዚህ እስራኤላውያንን፣ “የፍጡር ሁሉ ሕይወት ደሙ ነውና የማንኛውንም ፍጡር ደም አትብሉ፤ የበላው ሰው ሁሉ ተለይቶ ይጥፋ” አልኋቸው።
እስራኤላውያን የሚሠዉትን መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር የሚያመጡበት ምክንያት ይህ ነው። ይህንም ካህኑ ዘንድ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አምጥተው ለእግዚአብሔር የኅብረት መሥዋዕት በማድረግ ያቅርቡ።
“ ‘ማንኛውም ሰው በወር አበባዋ ጊዜ ከሴት ጋራ ግብረ ሥጋ ቢፈጽም፣ የፈሳሿን ምንጭ ገልጧልና፣ እርሷም የፈሳሿን ምንጭ ገልጣለችና ሁለቱም ከሕዝባቸው መካከል ተለይተው ይጥፉ።
ልጁን ለሞሎክ በመስጠት መቅደሴን አርክሷልና፣ ቅዱሱን ስሜንም አቃልሏልና፣ በዚያ ሰው ላይ ጠላት እሆንበታለሁ፤ ከወገኖቹም ለይቼ አጠፋዋለሁ።
በመሥዋዕቱ ራስ ላይ እጁን ይጫን፤ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ይረደው፤ ካህናቱም የአሮን ልጆች ደሙን በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ይርጩት።
ማንኛውም የኅብረት መሥዋዕት ሥጋ በሦስተኛው ቀን ከተበላ ተቀባይነት የለውም፤ ርኩስ በመሆኑ ላቀረበው ሰው ዋጋ አይኖረውም፤ ከዚያም የበላ ሰው የበደል ዕዳ ይሆንበታል።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ስለ ተቤዠኸው ሕዝብህ ስለ እስራኤል ብለህ ይህን ስርየት ተቀበል፤ ሕዝብህንም በፈሰሰው ንጹሕ ደም በደለኛ አታድርግ።” ስለ ፈሰሰውም ደም ስርየት ይደረግላቸዋል።