የእንበረም ወንዶች ልጆች፤ አሮን፣ ሙሴ። አሮን የተቀደሰ እንዲሆን ተለየ፤ እርሱና ዘሮቹ ለዘላለም ቅዱስ የሆኑትን ነገሮች እንዲቀድሱ፣ በእግዚአብሔር ፊት መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፣ በፊቱ እንዲያገለግሉና በስሙም ለዘላለም እንዲባርኩ ተለዩ።
ዘሌዋውያን 17:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለአሮንና ለልጆቹ፣ ለእስራኤላውያንም ሁሉ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘እግዚአብሔር ያዘዘው ይህ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለአሮንና ለልጆቹ ለእስራኤልም ልጆች ሁሉ ተናገር እንዲህም በላቸው፦ ጌታ ያዘዘው ቃል ይህ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ ‘እግዚአብሔር ያዘዘው ትእዛዝ ይህ ነው’ ብለህ ለአሮንና ለልጆቹ እንዲሁም ለእስራኤላውያን ሁሉ ንገር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለአሮንና ለልጆቹ፥ ለእስራኤልም ልጆች ሁሉ እንዲህ ብለህ ንገር፦ እግዚአብሔር ያዘዘው ይህ ነው፤ እንዲህም አለ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአሮንና ለልጆቹ ለእስራኤልም ልጆች ሁሉ እንዲህ ብለህ ንገር፦ እግዚአብሔር ያዘዘው ይህ ነው፥ እንዲህም አለ፦ |
የእንበረም ወንዶች ልጆች፤ አሮን፣ ሙሴ። አሮን የተቀደሰ እንዲሆን ተለየ፤ እርሱና ዘሮቹ ለዘላለም ቅዱስ የሆኑትን ነገሮች እንዲቀድሱ፣ በእግዚአብሔር ፊት መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፣ በፊቱ እንዲያገለግሉና በስሙም ለዘላለም እንዲባርኩ ተለዩ።