La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 8:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከከተማዪቱ በስተሰሜን የነበሩትንም፣ ከከተማዪቱ በስተምዕራብ የሸመቁትንም ወታደሮች ሁሉ ስፍራ ስፍራቸውን እንዲይዙ አደረጋቸው፤ በዚያችም ሌሊት ኢያሱ ወደ ሸለቆው ሄደ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በከተማይቱ በሰሜን በኩል የነበሩትን ሠራዊት ሁሉ በከተማይቱም በምዕራብ በኩል የኋላ ደጀን የሆነውን ሕዝብ አኖሩ፤ ኢያሱም በዚያች ሌሊት በሸለቆው ውስጥ አደረ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነርሱም ዋናውን ሠራዊት ከከተማ በስተሰሜን በኩል፥ የኋላውን ደጀን በስተምዕራብ በኩል አሰለፉ፤ ኢያሱ ግን ሌሊቱን በሸለቆው አሳለፈ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሕዝ​ቡም ሁሉ ሠራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን በከ​ተ​ማው መስዕ በኩል አኖሩ፤ ዳር​ቻ​ውም እስከ ከተ​ማው ባሕር ድረስ ነው፤ ኢያ​ሱም በዚ​ያች ሌሊት ወደ ሸለ​ቆው መካ​ከል ሄደ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በከተማይቱ በሰሜን በኩል የነበሩትን ሠራዊት ሁሉ በከተማይቱም በምዕራብ በኩል የተደበቁትን ሕዝብ አኖሩ፥ ኢያሱም በዚያች ሌሊት ወደ ሸለቆው መካከል ሄደ።

Ver Capítulo



ኢያሱ 8:13
3 Referencias Cruzadas  

ኢያሱ ቀደም ብሎ ዐምስት ሺሕ ሰው ያህል በመውሰድ ከከተማዪቱ በስተምዕራብ፣ በቤቴልና በጋይ መካከል እንዲያደፍጡ አድርጎ ነበር።


የጋይ ንጉሥ ይህን ባየ ጊዜ እርሱና የከተማዪቱ ወንዶች ሁሉ ማልደው በመገሥገሥ፣ እስራኤልን ለመውጋት ከዓረባ ፊት ለፊት ወደሚገኘው ስፍራ መጡ፤ ንጉሡ ግን ከከተማዪቱ በስተጀርባ ያደፈጠ ኀይል የሚጠባበቀው መሆኑን አያውቅም ነበር።


ከተማዪቱን ስትይዙም በእሳት አቃጥሏት፤ እግዚአብሔር ያዘዘውንም አድርጉ፤ እነሆ አዝዣችኋለሁ።”