ከገንዳው ከንፈር በታችም በእያንዳንዱ ክንድ ርቀት ላይ ዙሪያውን ዐሥር የኰርማ ቅርጾች ነበሩበት፤ ኰርማዎቹም ከገንዳው ጋራ አንድ ወጥ ሆነው በሁለት ረድፍ ቀልጠው ተሠርተው ነበር።
ኢያሱ 6:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከተማዪቱን ከተዋጊዎቻችሁ ጋራ አንድ ጊዜ ዙሩ፤ ይህንም ስድስት ቀን አድርጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተም ከተማይቱን ትዞሩአታላችሁ፥ ተዋጊዎቻችሁም ሁሉ ከተማይቱን በቀን አንድ ጊዜ ይዙሩአት፤ እንዲሁም ስድስት ቀን አድርጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተና ወታደሮችህ እስከ ስድስት ቀን ድረስ በቀን አንድ ጊዜ የከተማይቱን ቅጽር በሰልፍ ትዞሩአታላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተም ተዋጊዎችን ሁሉ በዙሪያው አሰልፋቸው። ተዋጊዎቻችሁም ሁሉ በከተማዪቱ ዙሪያ አንድ ጊዜ ይዙሩ፤ እንዲሁም ስድስት ቀን አድርጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰልፈኞቻችሁ ሁሉ ከተማይቱን አንድ ጊዜ ይዙሩአት፥ እንዲሁም ስድስት ቀን አድርጉ። |
ከገንዳው ከንፈር በታችም በእያንዳንዱ ክንድ ርቀት ላይ ዙሪያውን ዐሥር የኰርማ ቅርጾች ነበሩበት፤ ኰርማዎቹም ከገንዳው ጋራ አንድ ወጥ ሆነው በሁለት ረድፍ ቀልጠው ተሠርተው ነበር።
ብቻ በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እንደ እንጀራ እንጐርሳቸዋለንና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሯቸው። ጥላቸው ተገፍፏል፤ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋራ ነውና አትፍሯቸው።”
ሕዝቡንም፣ “ወደ ፊት ሂዱ፤ ከተማዋን ዙሩ፤ የታጠቁ ተዋጊዎችም በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ቀድመው ይሂዱ፤ ከተማዪቱንም ዙሩ” ሲል አዘዛቸው።