እግዚአብሔር ሆይ፤ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነውና፤ ታላቅነት፣ ኀይል፣ ክብርና ግርማ የአንተ ነው። እግዚአብሔር ሆይ፤ መንግሥትም የአንተ ነው፤ አንተም እንደ ራስ ከሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያልህ ነህ።
ኢያሱ 3:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ የምድር ሁሉ ጌታ የቃል ኪዳኑ ታቦት ቀድሟችሁ ወደ ዮርዳኖስ ይገባል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ የምድር ሁሉ ጌታ ቃል ኪዳን ታቦት በፊታችሁ ወደ ዮርዳኖስ ያልፋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምድር ሁሉ ጌታ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት በፊታችሁ ቀድሞ ወደ ዮርዳኖስ ማዶ ይሸጋገራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ የምድር ሁሉ ጌታ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት በፊታችሁ ዮርዳኖስን ትሻገራለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ የምድር ሁሉ ጌታ ቃል ኪዳን ታቦት በፊታችሁ ወደ ዮርዳኖስ ያልፋል። |
እግዚአብሔር ሆይ፤ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነውና፤ ታላቅነት፣ ኀይል፣ ክብርና ግርማ የአንተ ነው። እግዚአብሔር ሆይ፤ መንግሥትም የአንተ ነው፤ አንተም እንደ ራስ ከሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያልህ ነህ።
የሕዝቦች ሁሉ ንጉሥ ሆይ፤ አንተን የማይፈራ ማነው? ክብር ይገባሃልና። ከምድር ጠቢባን ሁሉ፣ ከመንግሥቶቻቸውም ሁሉ መካከል፣ እንደ አንተ ያለ የለም።
“የጽዮን ልጅ ሆይ፤ ተነሥተሽ አበራዪ፤ የብረት ቀንድ እሰጥሻለሁና፤ የናስ ሰኰና እሰጥሻለሁ፤ አሕዛብንም ታደቅቂአቸዋለሽ።” በግፍ ያግበሰበሱትን ትርፍ ለእግዚአብሔር፣ ሀብታቸውንም ለምድር ሁሉ ጌታ ትለዪአለሽ።
እግዚአብሔር የምድሪቱን አማልክት ሁሉ በሚደመስስበት ጊዜ፣ በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፤ በየባሕሩ ጠረፍ የሚኖሩ ሕዝቦች፣ እያንዳንዳቸው በያሉበት ሆነው ለርሱ ይሰግዳሉ።
ይሁን እንጂ እንደሚባላ እሳት ከፊትህ ቀድሞ የሚሻገረው አምላክህ እግዚአብሔር መሆኑን ዛሬ ርግጠኛ ሁን፤ እነርሱን ያጠፋቸዋል፤ በፊትህም ድል ያደርጋቸዋል፤ አንተም እግዚአብሔር በሰጠህ ተስፋ መሠረት ታስወጣቸዋለህ፤ በፍጥነትም ትደመስሳቸዋለህ።
የምድርን ሁሉ ጌታ የእግዚአብሔርን ታቦት የተሸከሙት ካህናት ገና እግራቸውን በዮርዳኖስ ውሃ ውስጥ እንዳስገቡ፣ ቍልቍል የሚወርደው ውሃ ወዲያውኑ ይቋረጣል፤ እንደ ክምርም ሆኖ ይቆማል።”