Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢያሱ 3:11 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እነሆ፥ የምድር ሁሉ ጌታ ቃል ኪዳን ታቦት በፊታችሁ ወደ ዮርዳኖስ ያልፋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እነሆ፤ የምድር ሁሉ ጌታ የቃል ኪዳኑ ታቦት ቀድሟችሁ ወደ ዮርዳኖስ ይገባል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እነሆ፥ የምድር ሁሉ ጌታ ቃል ኪዳን ታቦት በፊታችሁ ወደ ዮርዳኖስ ያልፋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የምድር ሁሉ ጌታ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት በፊታችሁ ቀድሞ ወደ ዮርዳኖስ ማዶ ይሸጋገራል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እነሆ፥ የም​ድር ሁሉ ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት በፊ​ታ​ችሁ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ትሻ​ገ​ራ​ለች።

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 3:11
15 Referencias Cruzadas  

አቤቱ፥ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነውና ታላቅነትና ኀይል፥ ክብርም፥ ድልና ግርማ ለአንተ ነው፤ አቤቱ፥ መንግሥት የአንተ ነው፤ አንተም በሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያልህ ራስ ነህ።


ከአፉ ፋናዎች ይወጣሉ፥ የእሳትም ፍንጣሪ ይረጫል።


ሕዝቤንስ አስገባሪዎቻቸው ይገፍፉአቸዋል፥ አስጨናቂዎችም ይሠለጥኑባቸዋል። ሕዝቤ ሆይ፥ የመሩአችሁ ያስቱአችኋል የምትሄዱበትንም መንገድ ያጠፋሉ።


ፈጣሪሽ ባልሽ ነው፥ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው፥ የእስራኤልም ቅዱስ ታዳጊሽ ነው፥ እርሱም የምድር ሁሉ አምላክ ይባላል።


የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ፥ በአሕዛብ ጥበበኞች ሁሉ መካከል በመንግሥታቸውም ሁሉ እንደ አንተ ያለ ስለሌለ፥ አንተን መፍራት ይገባልና አንተን የማይፈራ ማን ነው?


የጽዮን ልጅ ሆይ፥ ቀንድሽን ብረት፥ ጥፍርሽንም ናስ አደርጋለሁና ተነሺ አሂጂ፥ ብዙ አሕዛብንም ታደቅቂአለሽ፥ ትርፋቸውንም ለእግዚአብሔር፥ ሀብታቸውንም ለምድር ሁሉ ጌታ ትቀድሻለሽ።


እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ የተፈራ ይሆናል፥ የምድርንም አማልክት ሁሉ ያከሳቸዋል፥ በአሕዛብም ደሴቶች ሁሉ ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በስፍራቸው ሆነው ለእርሱ ይሰግዳሉ።


እግዚአብሔርም በምድር ሁሉ ላይ ይነግሣል፥ በዚያ ቀን እግዚአብሔር አንድ፥ ስሙም አንድ ይሆናል።


መልአኩም መልሶ፦ እነዚህ በምድር ሁሉ ጌታ ፊት ከቆሙበት ስፍራ የሚወጡ አራቱ የሰማይ ነፋስት ናቸው።


አምላክህም እግዚአብሔር እንደሚበላ እሳት ሆኖ በፊትህ እንዲያልፍ ዛሬ እወቅ፤ እርሱ ያጠፋቸዋል፥ በፊትህም ያዋርዳቸዋል፤ እግዚአብሔርም እንደ ነገረህ አንተ ታሳድዳቸዋለህ፥ ፈጥነህም ታጠፋቸዋለህ።


እንዲህም ይሆናል፥ የምድርን ሁሉ ጌታ የእግዚአብሔርን ታቦት የተሸከሙ ካህናት እግር ጫማ በዮርዳኖስ ውኃ ውስጥ ሲቆም፥ ከላይ የሚወርደው የዮርዳኖስ ውኃ ይቋረጣል፥ እንደ ክምርም ሆኖ ይቆማል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos