ኢያሱ 24:28 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ኢያሱ ሕዝቡን ሁሉ ወደየርስቱ እንዲሄድ አሰናበተ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም እያንዳንዱን ሰው ሕዝቡን ወደ ርስቱ እዲሄድ አደረገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኢያሱ ሕዝቡን ሁሉ አሰናበተ፤ እያንዳንዱም ወደየርስት ይዞታው ተመልሶ ሄደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም ሕዝቡን አሰናበተ፤ ሁሉም ወደየቦታቸው ገቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም ሕዝቡን በእያንዳንዱ ወደ ርስቱ ሰደደ። |
ኢያሱም ሕዝቡን ሁሉ፣ “እነሆ፤ ይህ ድንጋይ፣ እግዚአብሔር የተናገረንን ሁሉ ሰምቷል፣ በእኛም ይመሰክርብናል፤ እናንተም በአምላካችሁ ዘንድ እውነተኞች ሆናችሁ ባትገኙ ምስክር ይሆንባችኋል” አላቸው።