ኢያሱ 21:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከይሁዳና ከስምዖን ነገዶች ደግሞ ከዚህ በታች በስም የተጠቀሱትን ከተሞች በዕጣ መደቡላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከይሁዳም ልጆች ነገድ ከስምዖንም ልጆች ነገድ በስማቸው የተጠሩትን እነዚህን ከተሞች ሰጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከይሁዳና ከስምዖን ነገዶች በስም የተጠቀሱትን የሚከተሉትን ከተሞች ሰጡ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይሁዳም ልጆች ነገድ፥ የስምዖንም ልጆች ነገድ፥ የብንያምም ልጆች ነገድ በስማቸው የተጠሩትን እነዚህን ከተሞች ሰጡአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከይሁዳም ልጆች ነገድ ከስምዖንም ልጆች ነገድ በስማቸው የተጠሩትን እነዚህን ከተሞች ሰጡ። |
ዔድን፣ ሚንያሚን፣ ኢያሱ፣ ሸማያ፣ አማርያና ሴኬንያ በካህናቱ ከተሞች ተገኝተው፣ ለካህናት ወገኖቻቸው ለታላላቆቹም ሆነ ለታናናሾቹ፣ እንደየምድባቸው፣ በማከፋፈሉ ረገድ በታማኝነት ረዱት።
እነዚህም ከተሞች የሌዊ ልጆች፣ የቀዓት ጐሣዎች ለሆኑት ለአሮን ዝርያዎች ተመደቡ፤ ይህም የሆነው የመጀመሪያው ዕጣ ለእነርሱ ስለ ወጣላቸው ነበር፤
የመጀመሪያው ዕጣ ለቀዓት ዘሮች በየጐሣቸው ወጣ፤ የካህኑ የአሮን ዝርያዎች ለሆኑት ሌዋውያን ከይሁዳ፣ ከስምዖንና ከብንያም ነገዶች ዐሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ተመደቡላቸው።