ኢያሱ 19:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም ቀጣትን፣ ነህላልን፣ ሺምሮንን፣ ይዳላንና ቤተ ልሔምን ይጨምራል፤ እነዚህም ከነመንደሮቻቸው ዐሥራ ሁለት ከተሞች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀጣት፥ ነህላል፥ ሺምሮን፥ ይዳላ፥ ቤተልሔም፤ ዐሥራ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም ቃጣት፥ ናህላል፥ ሺምሮን፥ ይዳላና ቤተልሔም ተብለው የሚጠሩትን ዐሥራ ሁለት ከተሞችና በዙሪያቸው ያሉትን ታናናሽ ከተሞች ያጠቃልላል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቃጠናት፥ ናባሐል፥ ሲምዖን፥ ኢያሪሆ፥ ቤቴሜንም፤ ዐሥራ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀጣት፥ ነህላል፥ ሺምሮን፥ ይዳላ፥ ቤተ ልሔም፥ አሥራ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው። |
ዛብሎንም እንደዚሁ በቂድሮንና በነህሎል የነበሩትን በመካከላቸው የቀሩትን ከነዓናውያንን አላስወጣም፤ ነገር ግን የጕልበት ሥራ እንዲሠሩ አስገደዳቸው።
ከዚያም ሁለቱ ሴቶች እስከ ቤተ ልሔም ድረስ ተጓዙ፤ ቤተ ልሔም እንደ ደረሱም፣ በእነርሱ ምክንያት ከተማው በሙሉ ተተረማመሰ፤ ሴቶቹም፣ “ይህች ኑኃሚን ናትን?” በማለት ተገረሙ።