ኢያሱ 19:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሣሪድም ወደ ምሥራቅ በመታጠፍ፣ የፀሓይ መውጫ ወደ ሆነው አገር ወደ ኪስሎትታቦር በመዝለቅ እስከ ዳብራት ሄዶ ወደ ያፊዓ ያቀናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሣሪድም ወደ ፀሐይ መውጫ ወደ ምሥራቅ ወደ ኪስሎትታቦር ዳርቻ ዞረ፤ ወደ ዳብራትም ወጣ፥ ወደ ያፊዓም ደረሰ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሣሪድም ባሻገር በምሥራቅ በኩል ወደ ኪስሎት ታቦር አልፎ እስከ ዳብራትና እስከ ያፊዓ ይደርሳል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሴዱቅም ወደ ቤተ ሳሚስ ምሥራቅ ወደ ካሲሎቴት ዳርቻ ይዞራል፤ ወደ ዳቤሮትም ይወጣል፤ ወደ ፋንጊም ይደርሳል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሣሪድም ወደ ፀሐይ መውጫ ወደ ምሥራቅ ወደ ኪስሎትታቦር ዳርቻ ዞረ፥ |
ዲቦራ፣ በንፍታሌም ውስጥ ቃዴስ በተባለች ከተማ ይኖር የነበረውን የአቢኒኤምን ልጅ ባርቅን አስጠርታ እንዲህ አለችው፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ያዝሃል፤ ‘ተነሣ፤ ከንፍታሌምና ከዛብሎን ዐሥር ሺሕ ሰዎች ይዘህ ወደ ታቦር ተራራ ውጣ፤