በምሥራቅ በኩል ያለው ወሰናቸው ደግሞ የጨው ባሕር ሲሆን፣ ይህም የዮርዳኖስ ወንዝ እስከሚሠርግበት ይደርሳል። በሰሜን በኩል ያለው ወሰንም የዮርዳኖስ ወንዝ ከሚሠርግበት የባሕር ወሽመጥ ይነሣና
ኢያሱ 15:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሽቅብ ወደ ቤትሖግላ ይወጣል፤ ከዚያም በሰሜናዊው ቤትዓረባ በኩል አድርጎ የሮቤል ልጅ የቦሀን ድንጋይ እስካለበት ይደርሳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ድንበሩ ወደ ቤትሖግላ ወጣ፥ በቤትዓረባ በሰሜን በኩል አለፈ፥ ወደ ሮቤልም ልጅ ወደ ቦሀን ድንጋይ ወጣ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስከ ቤትሆግላ ይወጣል፤ ከዚያም በሰሜን በዮርዳኖስ ሸለቆ በኩል አልፎ የሮቤል ልጅ ወደ ሆነው ወደ ቦሐን መታሰቢያ ድንጋይ ድረስ ይወጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም ድንበራቸው ወደ ቤተ ገለዓም ይወጣል፤ በቤትዓረባ በሰሜን በኩል ያልፋል፤ ድንበራቸውም ወደ ሮቤል ልጅ ወደ ሊቶን ቢዮን ይወጣል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም ድንበሩ ወደ ቤትሖግላ ወጣ፥ በቤትዓረባ በሰሜን በኩል አለፈ፥ ወደ ሮቤልም ልጅ ወደ ቦሀን ድንጋይ ወጣ፥ |
በምሥራቅ በኩል ያለው ወሰናቸው ደግሞ የጨው ባሕር ሲሆን፣ ይህም የዮርዳኖስ ወንዝ እስከሚሠርግበት ይደርሳል። በሰሜን በኩል ያለው ወሰንም የዮርዳኖስ ወንዝ ከሚሠርግበት የባሕር ወሽመጥ ይነሣና
ከዚያም ድንበሩ ከአኮር ሸለቆ ወደ ዳቤር ይወጣና ከወንዙ በስተ ደቡብ ባለው በአዱሚም መተላለፊያ ፊት ለፊት አድርጎ በስተሰሜን ወደ ጌልገላ ይታጠፋል፤ በዓይንሳሚስ ምንጭ በኩል ዐልፎም ወደ ዓይንሮጌል ይወጣል።
ደግሞም ወደ ሰሜን ይታጠፍና በዓይንሳሚስ በኩል አድርጎ እስከ ጌሊሎት ይዘልቃል፤ ከዚያም በአዱሚም መተላለፊያ ትይዩ እስካለው እስከ ሮቤል ልጅ እስከ ቦሀን ድንጋይ ይወርዳል።