ስለ ይሁዳ የተናገረው ይህ ነው፦ “እግዚአብሔር ሆይ፤ የይሁዳን ጩኸት ስማ፤ ወደ ወገኖቹም አምጣው። በገዛ እጆቹ ራሱን ይከላከላል፤ አቤቱ ከጠላቶቹ ጋራ ሲዋጋ ረዳቱ ሁን!”
ኢያሱ 15:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለይሁዳ ነገድ በየጐሣቸው የተሰጣቸው ርስት ይህ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በየወገኖቻቸውም የይሁዳ ልጆች ነገድ ርስት ይህ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይሁዳ ነገድ በየወገናቸው የተቀበሉት የርስት ድርሻ ይህ ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በየወገኖቻቸውም የይሁዳ ልጆች ነገድ ርስት ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በየወገኖቻቸውም የይሁዳ ልጆች ነገድ ርስት ይህ ነው። |
ስለ ይሁዳ የተናገረው ይህ ነው፦ “እግዚአብሔር ሆይ፤ የይሁዳን ጩኸት ስማ፤ ወደ ወገኖቹም አምጣው። በገዛ እጆቹ ራሱን ይከላከላል፤ አቤቱ ከጠላቶቹ ጋራ ሲዋጋ ረዳቱ ሁን!”
እርሷም፣ “እባክህ፤ ባርከኝ፤ በኔጌብ መሬት እንደ ሰጠኸኝ ሁሉ፣ አሁንም የውሃ ምንጭ ጕድጓዶች ስጠኝ” አለችው፤ ካሌብም የላይኛውንና የታችኛውን ምንጮች ሰጣት።