ስለዚህ የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ፣ ሆሃም ወደተባለው የኬብሮን ንጉሥ ጲርአም ወደተባለው የያርሙት ንጉሥ፣ ያፊዓ ወደተባለው የለኪሶ ንጉሥና ዳቤር ወደተባለው የዔግሎን ንጉሥ በመላክ፣
ኢያሱ 15:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በዳቤር ሕዝብ ላይ ዘመተ፤ ዳቤር ቀድሞ ቂርያትሤፍር ትባል ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም በዳቤር ሰዎች ላይ ወጣ፤ የዳቤርም ስም አስቀድሞ ቂርያትሤፍር ትባል ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም ተነሥቶ በደቢር በሚኖሩት ሕዝብ ላይ አደጋ ለመጣል ሄደ፤ ይህች ከተማ ቀድሞ ቂርያትሴፌር ተብላ ትጠራ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም ካሌብ በዳቤር ሰዎች ላይ ዘመተ፤ የዳቤርም ስም አስቀድሞ “ሀገረ መጻሕፍት” ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም በዳቤር ሰዎች ላይ ወጣ፥ የዳቤርም ስም አስቀድሞ ቂርያትሤፍር ትባል ነበረ። |
ስለዚህ የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ፣ ሆሃም ወደተባለው የኬብሮን ንጉሥ ጲርአም ወደተባለው የያርሙት ንጉሥ፣ ያፊዓ ወደተባለው የለኪሶ ንጉሥና ዳቤር ወደተባለው የዔግሎን ንጉሥ በመላክ፣