ኢያሱ 12:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴና እስራኤላውያን እነዚህን ድል አደረጉ፤ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴም ምድራቸውን ለሮቤል፣ ለጋድና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት አድርጎ ሰጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ ባርያ ሙሴና የእስራኤል ልጆች አሸነፉአቸው፤ የጌታም ባርያ ሙሴ ርስት አድርጎ ለሮቤል ልጆች ለጋድም ልጆች ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ምድሪቱን ሰጣቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ እነዚህ ሁለት ነገሥታት በእግዚአብሔር አገልጋይ በሙሴና በእስራኤል ሕዝብ ጦርነት ድል ሆነው ነበር፤ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴም ይህን ምድር ለሮቤልና ለጋድ ነገዶች እንዲሁም ለምናሴ ነገድ እኩሌታ በማከፋፈል ርስት አድርጎ ሰጣቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴና የእስራኤል ልጆች ገደሉአቸው፤ የእግዚአብሔርም አገልጋይ ሙሴ ርስት አድርጎ ለሮቤል ልጆች፥ ለጋድም ልጆች፥ ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ምድሪቱን ሰጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴና የእስራኤል ልጆች መቱአቸው፥ የእግዚአብሔርም ባሪያ ሙሴ ርስት አድርጎ ለሮቤል ልጆች ለጋድም ልጆች ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ምድሪቱን ሰጣቸው። |
እንዲህም አላቸው፤ “የጋድና የሮቤል ወንድ ሁሉ፣ እያንዳንዱ ለጦርነት በመዘጋጀት በእግዚአብሔር ፊት ከእናንተ ጋራ ዮርዳኖስን የሚሻገር ከሆነ፣ ምድሪቱም በእጃችሁ ስትገባ የገለዓድን ምድር ርስት አድርጋችሁ ስጧቸው።
ከዚያም ሙሴ፣ የአሞራውያንን ንጉሥ የሴዎንን ግዛትና የባሳንን ንጉሥ የዐግን ግዛት፣ ማለትም ምድሪቱንና ከነከተሞቿ በዙሪያዋ ያለውን ግዛት በሙሉ ለጋድና ለሮቤል ነገዶች እንዲሁም ለዮሴፍ ልጅ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሰጣቸው።
ሌዋውያኑ ግን ለእግዚአብሔር የሚሰጡት የክህነት አገልግሎት ርስታቸው ስለ ሆነ በእናንተ መካከል ድርሻ አይኖራቸውም። ጋድ፣ ሮቤልና የምናሴ ነገድ እኩሌታም የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ በምሥራቅ ዮርዳኖስ የሰጣቸውን ርስት ቀደም አድርገው ወስደዋል።”
አሁንም አምላካችሁ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ተስፋ መሠረት ወንድሞቻችሁን አሳርፏቸዋል፤ ስለዚህ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ከዮርዳኖስ ማዶ ርስት አድርጎ በሰጣችሁ ምድር ወዳለው ቤታችሁ ተመለሱ።