ይህ የሆነው በሐሴቦን ይገዛ የነበረውን የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንና በአስታሮት ይገዛ የነበረውን የዐግን ንጉሥ ባሳንን በኤድራይ ድል ካደረገ በኋላ ነው።
ኢያሱ 12:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም መቀመጫውን በአስታሮትና በኤድራይ አድርጎ የገዛውና ከመጨረሻዎቹ ከራፋይም ዘሮች አንዱ የሆነው የባሳን ንጉሥ ዐግ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከራፋይምም ወገን የቀረ፥ በአስታሮትና በኤድራይ የተቀመጠው የባሳን ንጉሥ ዐግ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ከረፋያውያን ወገን የቀረው በአስታሮትና በኤድራይ ይኖር የነበረው የባሳን ንጉሥ ዖግ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከረዓይት ወገን የቀረ፥ በአስጣሮትና በኤንድራይን የተቀመጠው፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከራፋይምም ወገን የቀረ፥ በአስታሮትና በኤድራይ የተቀመጠው፥ የአርሞንዔምንም ተራራ፥ |
ይህ የሆነው በሐሴቦን ይገዛ የነበረውን የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንና በአስታሮት ይገዛ የነበረውን የዐግን ንጉሥ ባሳንን በኤድራይ ድል ካደረገ በኋላ ነው።
ይህም በአስታሮትና በኤድራይ ሆኖ የገዛውን በባሳን ያለውን የዐግን መንግሥት በሙሉ ያጠቃልላል፤ ዐግም በሕይወት ከቀሩት ከመጨረሻዎቹ ከራፋይም ዘሮች አንዱ ነበር። እነዚህንም ሙሴ ድል አደረጋቸው፤ ምድራቸውንም ያዘ፤
የገለዓድን እኩሌታ፣ በባሳን የዐግ መንግሥት ዋና ከተማ የሆኑትን አስታሮትንና ኤድራይን ይጨምራል። እነዚህ ለምናሴ ልጅ ለማኪር ዘሮች የተሰጡ ሲሆን፣ ይህም ለግማሾቹ የማኪር ልጆች በየጐሣቸው የተሰጡ ናቸው።