ኢዮሣፍጥና ሰዎቹም ምርኳቸውን ለማጋዝ ሄዱ፤ በዚያም መካከል እጅግ ብዙ መሣሪያና ልብስ፣ ሊሸከሙ ከሚችሉትም በላይ ውድ ዕቃዎችን አገኙ። ምርኮውም ከመብዛቱ የተነሣ ለመሰብሰብ ሦስት ቀን ፈጀ።
ኢያሱ 11:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን ምርኮውን በሙሉ፣ ከእነዚህም ከተሞች የተገኙትን እንስሳት ለራሳቸው ወሰዱ፤ ሕዝቡን ግን በሙሉ በሰይፍ ስለት ፈጁት፤ እስትንፋስ ካለው ፍጡር አንድም ሰው ሳያስቀር ፈጽመው ደመሰሱት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ልጆች የእነዚህን ከተሞች ምርኮ ሁሉ ከብቶቹንም ለራሳቸው ዘረፉ፤ ሰዎቹን ሁሉ ግን እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍ ስለት መቱአቸው፥ እስትንፋስ ያለውንም ሁሉ አላስቀሩም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ሕዝብ ዋጋ ያለውን ንብረትና ከብቱን ሁሉ ከእነዚህ ከተሞች ወስደው የራሳቸው ንብረት አደረጉት፤ ሰዎቹን ሁሉ ግን በሰይፍ ስለት ፈጽመው አጠፉ፤ አንድ ሰው እንኳ ሳይቀር ሁሉንም ገደሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች የእነዚህን ከተሞች ምርኮ ሁሉ፥ ከብቶቹንም ለራሳቸው ዘረፉ፤ ሰዎቹን ሁሉ ግን እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍ ስለት መቱአቸው፤ እስትንፋስ ያለውንም ሁሉ አንድም አላስቀሩም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች የእነዚህን ከተሞች ምርኮ ሁሉ ከብቶቹንም ለራሳቸው ዘረፉ፥ ሰዎቹን ሁሉ ግን እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍ ስለት መቱአቸው፥ እስትንፋስ ያለውንም ሁሉ አላስቀሩም። |
ኢዮሣፍጥና ሰዎቹም ምርኳቸውን ለማጋዝ ሄዱ፤ በዚያም መካከል እጅግ ብዙ መሣሪያና ልብስ፣ ሊሸከሙ ከሚችሉትም በላይ ውድ ዕቃዎችን አገኙ። ምርኮውም ከመብዛቱ የተነሣ ለመሰብሰብ ሦስት ቀን ፈጀ።
ከዚያም እስራኤላውያን የምድያማውያንን ሴቶችና ሕፃናት ማረኩ፤ የቀንድ ከብቶቻቸውን፣ የበግና የፍየል መንጋዎቻቸውን ሁሉ ነዱ፤ ሀብታቸውንም በሙሉ ወሰዱ።
ነገር ግን ሴቶቹን ሕፃናትን፣ እንስሳቱንና በከተማዪቱ ውስጥ የሚገኘውን ማንኛውንም ነገር በምርኮ ለራስህ አድርግ፤ አምላክህ እግዚአብሔር ከጠላቶችህ የሚሰጥህን ምርኮ ልትጠቀምበት ትችላለህ።
በዚህ ሁኔታም ኢያሱ ተራራማውን አገር ኔጌብን፣ የምዕራቡን ቈላና የተራራውን ሸንተረሮች ጨምሮ ምድሪቱን በሙሉ ከነገሥታቷ ጋራ ያዘ። የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ባዘዘውም መሠረት፣ እስትንፋስ ያላቸውን ሁሉ ፈጽሞ ደመሰሰ፤ ማንንም በሕይወት አላስቀረም።
በውስጧ ያሉትን ሁሉ በሰይፍ ስለት ገደሉ፤ እስትንፋስ ካለው ፍጡር አንድ እንኳ ሳያስቀሩ ሁሉንም ደመሰሱ፤ ራሷን አሦርንም በእሳት አቃጠሏት።
እግዚአብሔር ባሪያውን ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ፣ ሙሴም ኢያሱን አዘዘው፤ ኢያሱም እንዲሁ አደረገ፤ እግዚአብሔር ሙሴን ካዘዘው ሁሉ እርሱ ያልፈጸመው አንዳች ነገር አልነበረም።
በኢያሪኮና በንጉሧ ላይ ያደረግኸውንም ሁሉ፣ በጋይና በንጉሧ ላይ ትደግመዋለህ፤ በዚህ ጊዜ ግን ምርኮውንና ከብቱን ለራሳችሁ ታደርጉታላችሁ፤ ታዲያ ከከተማዪቱ በስተጀርባ የደፈጣ ጦር አዘጋጅ።”