ዮሐንስ 8:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አይሁድም፣ “ ‘እኔ ወደምሄድበት ልትመጡ አትችሉም’ ያለው ራሱን ሊገድል ይሆን?” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አይሁድም “‘እኔ ወደምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም፤’ ማለቱ እራሱን ሊገድል ይሆን?” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአይሁድ ባለሥልጣኖችም “ ‘እኔ ወደምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም’ ማለቱ ራሱን ሊገድል ይሆን?” ተባባሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አይሁድም፥ “እኔ ወደምሄድበት እናንተ መምጣት አትችሉም የሚለን እርሱ ራሱን ይገድል ይሆን? እንጃ!” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አይሁድም፦ “እኔ ወደ ምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም ማለቱ ራሱን ይገድላልን? እንጃ” አሉ። |
አይሁድም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፤ “ይህ ሰው፣ ልናገኘው የማንችለው ወዴት ለመሄድ ቢያስብ ነው? በግሪኮች መካከል ተበታትነው ወደሚኖሩት ወገኖቻችን ሄዶ ግሪኮችን ሊያስተምር ፈልጎ ይሆን?
አይሁድም እንዲህ አሉት፤ “ጋኔን እንዳለብህ አሁን ዐወቅን፤ አብርሃም ሞተ፤ ነቢያትም እንዲሁ፤ አንተ ግን ማንም ቃልህን ቢጠብቅ ሞትን ፈጽሞ እንደማይቀምስ ትናገራለህ።