Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዮሐንስ 8:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ኢየሱስም እንደ ገና፣ “እኔ እሄዳለሁ፤ እናንተም ትፈልጉኛላችሁ፤ በኀጢአታችሁም ትሞታላችሁ፤ እኔ ወደምሄድበት ግን ልትመጡ አትችሉም” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ኢየሱስም ደግሞ “እኔ እሄዳለሁ፤ ትፈልጉኛላችሁም፤ በኀጢአታችሁም ትሞታላችሁ፤ እኔ ወደምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም፤” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እንደገናም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “እኔ እሄዳለሁ፤ እናንተም እኔን ትፈልጉኛላችሁ፤ ነገር ግን ከነኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ እንጂ እኔ ወደምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ዳግ​መ​ኛም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ፥ “እኔ እሄ​ዳ​ለሁ ትሹ​ኛ​ላ​ች​ሁም፤ ነገር ግን አታ​ገ​ኙ​ኝም፤ በኀ​ጢ​ኣ​ታ​ች​ሁም ትሞ​ታ​ላ​ችሁ፤ እኔ ወደ​ም​ሄ​ድ​በ​ትም እና​ንተ መም​ጣት አይ​ቻ​ላ​ች​ሁም” አላ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ኢየሱስም ደግሞ፦ “እኔ እሄዳለሁ ትፈልጉኛላችሁም በኃጢአታችሁም ትሞታላችሁ እኔ ወደምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 8:21
21 Referencias Cruzadas  

አምላክህን ሕያው እግዚአብሔርን! ጌታዬ አንተን ለመፈለግ መልእክተኛ ያልላከበት ሕዝብና መንግሥት የለም፤ የትኛውም ሕዝብ ሆነ መንግሥት አንተ በዚያ አለመኖርህን ባስታወቀው ጊዜ ሁሉ አንተን አለማግኘቱን ለማረጋገጥ ያስምለው ነበር።


ዐጥንቱን የሞላው የወጣትነት ብርታት፣ ከርሱ ጋራ በዐፈር ውስጥ ይተኛል።


ክፉ ሰው ሲሞት ተስፋው ከንቱ ትሆናለች፤ በኀይሉ የተመካበትም ሁሉ እንዳልነበረ ይሆናል።


ክፉዎች በክፋታቸው ይወድቃሉ፤ ጻድቃን ግን በሞት ጊዜ እንኳ መጠጊያ አላቸው።


“ከእንግዲህም በዚያ፣ ለጥቂት ጊዜ ብቻ በሕይወት የሚኖር ሕፃን፣ ወይም ዕድሜ ያልጠገበ አረጋዊ አይኖርም፤ አንድ መቶ ዓመት የሞላው ሰው ቢሞት፣ በዐጭር እንደ ተቀጨ ይቈጠራል፤ አንድ ሰው መቶ ዓመት ሳይሞላው ቢሞት፣ እንደ ተቀሠፈ ይገመታል።


እላችኋለሁና፤ ‘በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው’ እስከምትሉ ድረስ ዳግመኛ አታዩኝም።”


“ከዚያም በግራው በኩል ላሉት ደግሞ እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እናንተ የተረገማችሁ፤ ለዲያብሎስና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀው የዘላለም እሳት ከእኔ ተለይታችሁ ሂዱ፤


“እነዚህም ወደ ዘላለም ፍርድ፣ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።”


ይህን የተናገረው በምን ዐይነት ሞት እንደሚሞት ለማመልከት ነበር።


ኢየሱስም እንዲህ ሲል ተናገራቸው፤ “ከእንግዲህ ለጥቂት ጊዜ ብርሃን አለላችሁ፤ ጨለማ ሳይመጣባችሁ፣ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማ የሚመላለስ ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም።


“ልጆቼ ሆይ፤ ከእናንተ ጋራ የምቈየው ለጥቂት ጊዜ ነው፤ እናንተም ትፈልጉኛላችሁ፤ ለአይሁድ፣ ‘እኔ ወደምሄድበት ልትመጡ አትችሉም’ እንዳልኋቸው፣ አሁንም ለእናንተ ይህንኑ እላችኋለሁ።


ትፈልጉኛላችሁ፤ ግን አታገኙኝም፤ እኔ ወዳለሁበትም ልትመጡ አትችሉም።”


‘ትፈልጉኛላችሁ፤ ግን አታገኙኝም፤ እኔ ወዳለሁበትም ልትመጡ አትችሉም’ ሲል ምን ማለቱ ይሆን?”


በኀጢአታችሁ እንደምትሞቱ ነግሬአችኋለሁ፤ እኔ እርሱ ነኝ ስላችሁ እኔ እርሱ እንደ ሆንሁ ካላመናችሁ፣ በኀጢአታችሁ ትሞታላችሁና።”


እናንተም በበደላችሁና በኀጢአታችሁ ምክንያት ሙታን ነበራችሁ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos