ዮሐንስ 4:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳሩ ግን ያጠመቀው ኢየሱስ ሳይሆን ደቀ መዛሙርቱ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምንም እንኳን ደቀመዛሙርቱ እንጂ ኢየሱስ እራሱ ባያጠምቅም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሆኖም ያጠምቁ የነበሩት የእርሱ ደቀ መዛሙርት እንጂ እርሱ ራሱ አያጠምቅም ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ደቀ መዛሙርቱ እንጂ እርሱ ራሱ ጌታችን ኢየሱስ አላጠመቀም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይሁዳን ትቶ ወደ ገሊላ ደግሞ ሄደ፤ ዳሩ ግን ደቀ መዛሙርቱ እንጂ ኢየሱስ ራሱ አላጠመቀም። |
ወደ ዮሐንስም መጥተው፣ “ረቢ፤ በዮርዳኖስ ማዶ ከአንተ ጋራ የነበረው፣ ስለ እርሱም የመሰከርህለት ሰው እነሆ፤ ያጠምቃል። ሰውም ሁሉ ወደ እርሱ እየሄደ ነው” አሉት።