በመጣሁ ጊዜ ለምን በዚያ ሰው አልነበረም? በተጣራሁስ ጊዜ የሚመልስ ሰው እንዴት በዚያ ታጣ? ስለ እናንተ ወጆ ለመክፈል ክንዴ ዐጥራ ነበርን? እናንተንስ ለማዳን ኀይል አነሰኝን? እነሆ፤ በተግሣጼ ባሕሩን አደርቃለሁ፤ ወንዞችን ምድረ በዳ አደርጋለሁ፤ ዓሦቻቸው ውሃ በማጣት ይሸታሉ፤ በጥማትም ይሞታሉ።
ዮሐንስ 3:32 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያየውንና የሰማውን ይመሰክራል፤ ነገር ግን ምስክርነቱን ማንም አይቀበልም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያየውንና የሰማውንም ይህን ይመሰክራል፤ ምስክርነቱንም የሚቀበለው የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ያየውንና የሰማውን ይመሰክራል፤ ነገር ግን የእርሱን ምስክርነት የሚቀበል የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባየውና በሰማው ይመሰክራል፤ ነገር ግን ምስክርነቱን የሚቀበለው የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያየውንና የሰማውንም ይህን ይመሰክራል፥ ምስክሩንም የሚቀበለው የለም። |
በመጣሁ ጊዜ ለምን በዚያ ሰው አልነበረም? በተጣራሁስ ጊዜ የሚመልስ ሰው እንዴት በዚያ ታጣ? ስለ እናንተ ወጆ ለመክፈል ክንዴ ዐጥራ ነበርን? እናንተንስ ለማዳን ኀይል አነሰኝን? እነሆ፤ በተግሣጼ ባሕሩን አደርቃለሁ፤ ወንዞችን ምድረ በዳ አደርጋለሁ፤ ዓሦቻቸው ውሃ በማጣት ይሸታሉ፤ በጥማትም ይሞታሉ።
ከእንግዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባሪያ ጌታው የሚሠራውን አያውቅምና፤ ነገር ግን ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ስለ ገለጽሁላችሁ ወዳጆች ብያችኋለሁ።
ጲላጦስም፣ “ታዲያ፣ ንጉሥ ነህ ማለት ነዋ!” አለው። ኢየሱስም፣ “እኔ ንጉሥ እንደ ሆንሁ መናገርህ ትክክል ነው፤ የተወለድሁት፣ ወደዚህም ዓለም የመጣሁት ስለ እውነት ለመመስከር ነው፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ይሰማኛል” አለው።
ወደ ዮሐንስም መጥተው፣ “ረቢ፤ በዮርዳኖስ ማዶ ከአንተ ጋራ የነበረው፣ ስለ እርሱም የመሰከርህለት ሰው እነሆ፤ ያጠምቃል። ሰውም ሁሉ ወደ እርሱ እየሄደ ነው” አሉት።