ዮሐንስ 19:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጲላጦስም ኢየሱስን ወስዶ አስገረፈው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜም ጲላጦስ ኢየሱስን ወስዶ ገረፈው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ጲላጦስ ኢየሱስን ወስዶ አስገረፈው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ ጲላጦስ ጌታችን ኢየሱስን ይዞ ገረፈው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜም ጲላጦስ ኢየሱስን ይዞ ገረፈው። |
ነገር ግን እርሱ ስለ መተላለፋችን ተወጋ፤ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ በርሱ ላይ የወደቀው ቅጣት ለእኛ ሰላም አመጣልን፤ በርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።
ስለዚህ ነቢያትን፣ ጠቢባንንና መምህራንን እልክላችኋለሁ፤ ከነዚህም አንዳንዶቹን ትገድላላችሁ፤ አንዳንዶቹን ትሰቅላላችሁ፤ ሌሎቹንም በምኵራቦቻችሁ ትገርፏቸዋላችሁ፤ ከከተማ ወደ ከተማ ታሳድዷቸዋላችሁ።