አዛሄልም፣ “ለመሆኑ እንደ ውሻ የሚቈጠር አገልጋይህ ይህን ጀብዱ መፈጸም እንዴት ይችላል?” አለ። ኤልሳዕም መልሶ፣ “መቼም አንተ በሶርያ ላይ እንደምትነግሥ እግዚአብሔር አሳይቶኛል” አለው።
ኢዩኤል 2:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሰሜንን ሰራዊት ከእናንተ አርቃለሁ፤ ፊቱን ወደ ምሥራቁ ባሕር፣ ጀርባውንም ወደ ምዕራቡ ባሕር በማድረግ፣ ወደ ደረቀውና ወደ ባድማው ምድር እገፋዋለሁ፤ ግማቱ ይወጣል፤ ክርፋቱም ይነሣል።” በርግጥ እርሱ ታላቅ ነገር አድርጓል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰሜንንም ሠራዊት ከእናንተ ዘንድ አርቃለሁ፥ ወደ በረሃና ወደ ምድረ በዳ፥ ፊቱን ወደ ምሥራቁ ባሕር ጀርባውንም ወደ ምዕራቡ ባሕር አድርጌ አሳድደዋለሁ፥ እርሱም ብዙ ነገር አድርጎአልና ግማቱ ይወጣል፥ ክርፋቱም ይነሣል አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሰሜን የሚመጣባችሁን የአንበጣ መንጋ ከእናንተ አርቅላችኋለሁ፤ ወደ በረሓና ወደ ምድረ በዳም አባርርላችኋለሁ፤ ግንባር ቀደም የሆኑትን ወደ ሙት ባሕር፥ በስተኋላ ያሉትን ወደ ሜዲቴራኒያን ባሕር እሰድላችኋለሁ፤ በዚያም በድናቸው ይከረፋል፤ በእርግጥ እኔ እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አድርጌላችኋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰሜንንም ሠራዊት ከእናንተ ዘንድ አርቃለሁ፤ ወደ በረሃና ወደ ምድረ በዳ እሰደዋለሁ፤ ፊቱን ወደ መጀመሪያው ባሕር፥ ጀርባውንም ወደ ኋለኛው ባሕር አድርጌ አሳድደዋለሁ፤ እርሱም ትዕቢትን አድርጎአልና ግማቱ ይወጣል፤ ክርፋቱም ይነሣል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰሜንንም ሠራዊት ከእናንተ ዘንድ አርቃለሁ፥ ወደ በረሃና ወደ ምድረ በዳ፥ ፊቱን ወደ ምሥራቁ ባሕር ጀርባውንም ወደ ምዕራቡ ባሕር አድርጌ አሳድደዋለሁ፥ እርሱም ትዕቢትን አድርጎአልና ግማቱ ይወጣል፥ ክርፋቱም ይነሣል አለ። |
አዛሄልም፣ “ለመሆኑ እንደ ውሻ የሚቈጠር አገልጋይህ ይህን ጀብዱ መፈጸም እንዴት ይችላል?” አለ። ኤልሳዕም መልሶ፣ “መቼም አንተ በሶርያ ላይ እንደምትነግሥ እግዚአብሔር አሳይቶኛል” አለው።
ከዚያም እግዚአብሔር ነፋሱን ወደ ብርቱ የምዕራብ ነፋስ ለወጠው፤ ያም ነፋስ አንበጣዎቹን እየነዳ ወደ ቀይ ባሕር ከተታቸው፤ በግብጽ ምድር በየትኛውም ቦታ አንድም አንበጣ አልቀረም።
በምሥራቅ በኩል ወሰኑ በሐውራንና በደማስቆ መካከል፣ በገለዓድና በእስራኤል ምድር መካከል ዮርዳኖስ ይሆናል፤ የምሥራቁ ድንበር እስከ ምሥራቁ ባሕር ይወርድና እስከ ታማር ይዘልቃል፤ ይህም የምሥራቁ ወሰን ይሆናል።
“በግብጽ ላይ እንዳደረግሁት፣ መቅሠፍትን ላክሁባችሁ፤ ከተማረኩት ፈረሶቻችሁ ጋራ፣ ጕልማሶቻችሁን በሰይፍ ገደልሁ፤ የሰፈራችሁ ግማት አፍንጫችሁ እንዲገባ አደረግሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም” ይላል እግዚአብሔር።
በዚያ ቀን የሕይወት ውሃ ከኢየሩሳሌም ይፈልቃል፤ እኩሌታው ወደ ምሥራቁ ባሕር፣ እኩሌታውም ወደ ምዕራቡ ባሕር ይፈስሳል፤ ይህም በበጋና በክረምት ይሆናል።
ስለ እናንተ ተባዩን እገሥጻለሁ፤ አዝመራችሁን አይበላም፤ ዕርሻ ላይ ያለ የወይን ተክላችሁም ፍሬ አልባ አይሆንም” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
በእግራችሁ የምትረግጡት ስፍራ ሁሉ የእናንተ ይሆናል፤ ግዛታችሁም ከምድረ በዳው እስከ ሊባኖስ፣ ከኤፍራጥስ ወንዝ አንሥቶ በስተምዕራብ እስካለው ባሕር ይደርሳል።