ኢዩኤል 2:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 የሰሜንንም ሠራዊት ከእናንተ ዘንድ አርቃለሁ፤ ወደ በረሃና ወደ ምድረ በዳ እሰደዋለሁ፤ ፊቱን ወደ መጀመሪያው ባሕር፥ ጀርባውንም ወደ ኋለኛው ባሕር አድርጌ አሳድደዋለሁ፤ እርሱም ትዕቢትን አድርጎአልና ግማቱ ይወጣል፤ ክርፋቱም ይነሣል።” Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም20 “የሰሜንን ሰራዊት ከእናንተ አርቃለሁ፤ ፊቱን ወደ ምሥራቁ ባሕር፣ ጀርባውንም ወደ ምዕራቡ ባሕር በማድረግ፣ ወደ ደረቀውና ወደ ባድማው ምድር እገፋዋለሁ፤ ግማቱ ይወጣል፤ ክርፋቱም ይነሣል።” በርግጥ እርሱ ታላቅ ነገር አድርጓል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 የሰሜንንም ሠራዊት ከእናንተ ዘንድ አርቃለሁ፥ ወደ በረሃና ወደ ምድረ በዳ፥ ፊቱን ወደ ምሥራቁ ባሕር ጀርባውንም ወደ ምዕራቡ ባሕር አድርጌ አሳድደዋለሁ፥ እርሱም ብዙ ነገር አድርጎአልና ግማቱ ይወጣል፥ ክርፋቱም ይነሣል አለ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 ከሰሜን የሚመጣባችሁን የአንበጣ መንጋ ከእናንተ አርቅላችኋለሁ፤ ወደ በረሓና ወደ ምድረ በዳም አባርርላችኋለሁ፤ ግንባር ቀደም የሆኑትን ወደ ሙት ባሕር፥ በስተኋላ ያሉትን ወደ ሜዲቴራኒያን ባሕር እሰድላችኋለሁ፤ በዚያም በድናቸው ይከረፋል፤ በእርግጥ እኔ እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አድርጌላችኋለሁ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 የሰሜንንም ሠራዊት ከእናንተ ዘንድ አርቃለሁ፥ ወደ በረሃና ወደ ምድረ በዳ፥ ፊቱን ወደ ምሥራቁ ባሕር ጀርባውንም ወደ ምዕራቡ ባሕር አድርጌ አሳድደዋለሁ፥ እርሱም ትዕቢትን አድርጎአልና ግማቱ ይወጣል፥ ክርፋቱም ይነሣል አለ። Ver Capítulo |