ኢዩኤል 1:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የልጅነት ዕጮኛዋን እንዳጣች ድንግል፣ ማቅ ለብሳችሁ አልቅሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እጮኛዋ ስለሞተባት ማቅ ለብሳ እንደምታለቅስ ድንግል አልቅሺ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እጮኛዋ ስለ ሞተባት ማቅ ለብሳ እንደምታለቅስ ልጃገረድ እናንተም አልቅሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ልጅነት ባልዋ ማቅ ለብሳ እንደምታለቅስ ድንግል አልቅሺ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለቍንጅናዋ ባል ማቅ ለብሳ እንደምታለቅስ ድንግል አልቅሺ። |
እናንተ ትዕቢት የወጠራችሁ ሴቶች ተንቀጥቀጡ፤ እናንተ ተደላድላችሁ የምትኖሩ ሴቶች ልጆች፣ በፍርሀት ተርበትበቱ! ልብሳችሁን አውልቁ፤ ወገባችሁን በማቅ ታጠቁ።
የጽዮን መንገዶች ያለቅሳሉ፤ በዓላቷን ለማክበር የሚመጣ የለምና፤ በበሮቿ ሁሉ የሚገባና የሚወጣ የለም፤ ካህናቷ ይቃትታሉ፤ ደናግሏ ክፉኛ ዐዝነዋል፤ እርሷም በምሬት ትሠቃያለች።
ዓመት በዓላችሁን ወደ ልቅሶ፣ ዝማሬአችሁንም ሁሉ ወደ ዋይታ እለውጣለሁ፤ ሁላችሁም ማቅ እንድትለብሱ፣ ጠጕራችሁንም እንድትላጩ አደርጋለሁ፤ ያን ጊዜ ለአንድያ ልጅ ሞት እንደሚለቀስበት፣ ፍጻሜውንም እንደ መራራ ቀን አደርገዋለሁ።”
እግዚአብሔር አንድ አላደረጋቸውምን? በሥጋም በመንፈስም የርሱ ናቸው። ለምን አንድ አደረጋቸው? ፈሪሀ እግዚአብሔር ያለውን ዘር ይፈልግ ስለ ነበር ነው። ስለዚህ በመንፈሳችሁ ራሳችሁን ጠብቁ፤ ከወጣትነት ሚስታችሁም ጋራ ያላችሁን ታማኝነት አታጓድሉ።