ኤርምያስ 8:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሐዘኔ የምታጽናናኝ ሆይ፤ ልቤ በውስጤ ዝላለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኀዘኔ የማይጽናና ነው፥ ልቤም በውስጤ ደክሞአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መጽናናት የማይገኝለት ብርቱ ሐዘን ደርሶብኛል፤ ልቤም እጅግ ዝሎአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልባችሁን ታምማችሁ ትቅበዘበዛላችሁ። ከሚያቅበዘብዝ የልብ ሕመማችሁ የሚያድናችሁ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኀዘኔ የማይጽናና ነው፥ ልቤም በውስጤ ደክሞአል። |
ስለ ነቢያት፣ ልቤ በውስጤ ተሰብሯል፤ ዐጥንቶቼም ተብረክርከዋል፤ ከእግዚአብሔር የተነሣ፣ ከቅዱስ ቃሉም የተነሣ፣ የወይን ጠጅ እንዳሸነፈው፣ እንደ ሰካራም ሰው ሆኛለሁ።
ወይ አበሳዬ! ወይ አበሳዬ! ሥቃይ በሥቃይ ላይ ሆነብኝ፤ አወይ፣ የልቤ ጭንቀት! ልቤ ክፉኛ ይመታል፤ ዝም ማለት አልችልም፤ የመለከትን ድምፅ፣ የጦርነትንም ውካታ ሰምቻለሁና።
እኔ ሰማሁ፤ ልቤም ደነገጠብኝ፤ ከንፈሬ ከድምፁ የተነሣ ተንቀጠቀጠ፤ ፍርሀት እስከ ዐጥንቴ ዘልቆ ገባ፤ እግሬም ተብረከረከ፤ ሆኖም በሚወርረን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ፣ የጥፋትን ቀን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ።