እግዚአብሔርም በኢዮአቄም ላይ ባቢሎናውያን፣ ሶርያውያን፣ ሞዓባውያንና አሞናውያን አደጋ ጣዮችን ላከበት፤ በአገልጋዮቹ በነቢያቱ አማካይነት በተነገረው በእግዚአብሔር ቃል መሠረት ይሁዳን ያጠፉ ዘንድ እነዚህን ላከ።
ኤርምያስ 6:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እረኞች መንጎቻቸውን ይዘው ይመጡባታል፤ ድንኳናቸውን በዙሪያዋ ይተክላሉ፤ እያንዳንዳቸውም በየአቅጣጫቸው መንጋቸውን ያሰማራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እረኞችና መንጐቻቸው ወደ እርሷ ይመጣሉ፥ በዙሪያዋም ድንኳኖቻቸውን ይተክሉባታል፥ እያንዳንዱም በስፍራው መንጋውን ያሰማራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እረኞች ከነመንጋቸው እዚያ ይሰፍራሉ፤ ድንኳኖቻቸውን በከተማይቱ ዙሪያ ይተክላሉ፤ እያንዳንዱም ደስ ባለው ስፍራ መንጋውን ያሰማራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እረኞችና መንጎቻቸው ወደ እርስዋ ይመጣሉ፤ በዙሪያዋም ድንኳኖቻቸውን ይተክሉባታል፤ በእጃቸውም መንጋቸውን ያሰማራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እረኞችና መንጐቻቸው ወደ እርስዋ ይመጣሉ፥ በዙሪያዋም ድንኳኖቻቸውን ይተክሉባታል፥ እያንዳንዱም በስፍራው መንጋውን ያሰማራል። |
እግዚአብሔርም በኢዮአቄም ላይ ባቢሎናውያን፣ ሶርያውያን፣ ሞዓባውያንና አሞናውያን አደጋ ጣዮችን ላከበት፤ በአገልጋዮቹ በነቢያቱ አማካይነት በተነገረው በእግዚአብሔር ቃል መሠረት ይሁዳን ያጠፉ ዘንድ እነዚህን ላከ።