ኤርምያስ 6:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀስትና ጦር ይዘዋል፤ ጨካኞችና ምሕረት የለሽ ናቸው፤ ፈረሶቻቸውን ሲጋልቡ፣ ድምፃቸው እንደ ተናወጠ ባሕር ነው፤ የጽዮን ልጅ ሆይ፤ ለሰልፍ የታጠቁ ሆነው፣ ሊወጉሽ ይመጣሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀስትንና ጦርን ይይዛሉ፤ ጨካኞች ናቸው፥ ምሕረትንም አያደርጉም፤ ድምፃቸው እንደ ባሕር ሞገድ ይጮኻል፥ በፈረሶችም ላይ ይቀመጣሉ፤ የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ! ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ሰው እያንዳንዳቸው በአንቺ ላይ ተሰለፉ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀስታቸውንና ሰይፋቸውን አንሥተዋል፤ እነርሱም ምሕረት የሌላቸው ጨካኞች ናቸው፤ ተቀምጠው የሚጋልቡአቸው ፈረሶች፥ የኮቴአቸው ድምፅ እንደ ባሕር ሞገድ ነው። እነሆ እነርሱ ኢየሩሳሌምን ለመውጋት ተዘጋጅተዋል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀስትንና ጦርን ይይዛሉ፤ ጨካኞች ናቸው፤ ምሕረትም አያደርጉም፤ ድምፃቸው እንደ ባሕር ሞገድ ይተምማል፤ በሰረገላና በፈረሶችም ላይ ይቀመጣሉ፤ የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ! እንደ እሳት ያጠፉሻል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀስትንና ጦርን ይይዛሉ፥ ጨካኞች ናቸው፥ ምሕረትንም አያደርጉም፥ ድምፃቸው እንደ ባሕር ይተምማል፥ በፈረሶችም ላይ ይቀመጣሉ፥ የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፥ ለሰልፍ እንደ ተዘጋጀ ሰው እያንዳንዳቸው በአንቺ ላይ ተሰለፉ። |
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ ጥፋት፣ ከአገር ወደ አገር እየተዛመተ መጥቷል፤ ብርቱ ዐውሎ ነፋስ፣ ከምድር ዳርቻ ተነሥቷል።”
የሰሜንን ሕዝብ ሁሉ፣ አገልጋዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እጠራለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “በዚህች ምድርና በነዋሪዎቿም ላይ፣ በአካባቢዋም ባሉ ሕዝቦች ሁሉ ላይ አመጣባቸዋለሁ፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፤ ሰዎች የሚጸየፏቸውና የሚሣለቁባቸው፣ የዘላለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ፤
ወዳጆችህ ሁሉ ረስተውሃል፤ ስለ አንተም ግድ የላቸውም። ጠላት እንደሚመታ መታሁህ፤ እንደ ጨካኝም ቀጣሁህ፤ በደልህ ታላቅ፣ ኀጢአትህም ብዙ ነውና።
“ይህን ለሕዝቦች አሳውቁ፤ ለኢየሩሳሌምም እንዲህ ብላችሁ በይፋ ንገሩ፤ ‘ከብበው የሚያስጨንቁ ከሩቅ አገር ይመጣሉ፤ በይሁዳ ከተሞችም ላይ ይደነፋሉ፤
ከፈረሰኞችና ከቀስተኞች ጩኸት የተነሣ፣ ከተማ ሁሉ ይሸሻል፤ አንዳንዶች ደን ውስጥ ይገባሉ፤ ሌሎችም ቋጥኝ ላይ ይወጣሉ፤ ከተሞች ሁሉ ባዶ ቀርተዋል፤ የሚኖርባቸውም የለም።
ቀስትና ጦር ይዘዋል፤ ጨካኞች ናቸው፤ ምሕረትም አያደርጉም፤ በፈረሳቸው እየጋለቡ ሲመጡ፣ ድምፃቸው እንደ ባሕር ሞገድ ይተምማል፤ ያስገመግማል። አንቺ የባቢሎን ሴት ልጅ ሆይ፤ ለጦርነት እንደ ተዘጋጁ ተዋጊዎች ይመጡብሻል።
የጠላት ፈረሶች ፉርፉርታ፣ ከዳን ይሰማል፤ በድንጉላ ፈረሶቻቸው ማሽካካት፣ መላዋ ምድር ተንቀጠቀጠች። ምድሪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ፣ ከተማዪቱንና በውስጧ የሚኖሩትን ሁሉ፣ ሊውጡ መጡ።