ኤርምያስ 51:60 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤርምያስ ስለ ባቢሎን ጽፎ ያስቀመጠውን ሁሉ፣ በባቢሎን ላይ የሚመጣውን ጥፋት ሁሉ በብራና ጥቅልል ላይ ጻፈው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በባቢሎንም ላይ የሚመጣውን ክፉ ነገር ሁሉ፥ ስለ ባቢሎን የተጻፈውን ይህን ቃል ሁሉ፥ ኤርምያስ በመጽሐፍ ላይ ጻፈው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በባቢሎን ላይ የሚመጣውን ጥፋት እንዲሁም ስለ እርስዋ የተነገረውን ቃል በመጽሐፍ ጻፍኩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሠራያም የቤቱ አዛዥ ነበረ፤ በባቢሎንም ላይ የሚመጣውን ክፉ ነገር ሁሉ፥ ስለ ባቢሎን የተጻፈውን ይህን ቃል ሁሉ ኤርምያስ በአንድ መጽሐፍ ላይ ጻፈው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በባቢሎንም ላይ የሚመጣውን ክፉ ነገር ሁሉ፥ ስለ ባቢሎን የተጻፈውን ይህን ቃል ሁሉ፥ ኤርምያስ በመጽሐፍ ላይ ጻፈው። |
ኤርምያስም ሌላ ብራና ወስዶ ለኔርያ ልጅ ለጸሓፊው ለባሮክ ሰጠው፤ ባሮክም የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአቄም በእሳት ባቃጠለው ብራና ላይ የነበረውን ቃል ሁሉ ከኤርምያስ አፍ ተቀብሎ ጻፈበት፤ ብዙ ተመሳሳይ ቃልም ተጨመረበት።
ዳንኤል ሆይ፤ አንተ ግን፣ እስከ ፍጻሜው ዘመን ድረስ የመጽሐፉን ቃል ዝጋ፤ ዐትመውም። ብዙዎች ወዲያ ወዲህ ይራወጣሉ፤ ዕውቀትም ይበዛል።”
ድምፁም፣ “የምታየውን በጥቅልል መጽሐፍ ጽፈህ በኤፌሶን፣ በሰምርኔስ፣ በጴርጋሞን፣ በትያጥሮን፣ በሰርዴስ፣ በፊላድልፍያና በሎዶቅያ ወደሚገኙት ወደ ሰባቱ የእስያ አብያተ ክርስቲያናት ላክ” አለ።