ኤርምያስ 51:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድራቸው በእስራኤል ቅዱስ ፊት፣ በበደል የተሞላች ብትሆንም፣ እስራኤልንና ይሁዳን አምላካቸው የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር አልጣላቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድራቸው በእስራኤል ቅዱስ ላይ በተሠራው በደል ምንም እንኳ የተሞላች ብትሆን፥ እስራኤልም ሆነ ይሁዳ በአምላካቸው በሠራዊት ጌታ ዘንድ አልተተዉም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድራቸው በእኔ በእስራኤል ቅዱስ ዘንድ በበደል የተሞላች ብትሆንም እንኳ እኔ የሠራዊት ጌታ አምላካቸው እስራኤልንና ይሁዳን አልረሳኋቸውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ምድራቸው በእስራኤል ቅዱስ ላይ በተሠራው በደል የተሞላች ብትሆንም፥ እስራኤል መበለት አልሆነችም፤ ይሁዳም ከአምላኩ ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ አልራቀም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድራቸው በእስራኤል ቅዱስ ላይ በተሠራው በደል ምንም እንኳ የተሞላች ብትሆን፥ እስራኤልም ሆነ ይሁዳ በአምላኩ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ዘንድ አልተጣለም። |
ይልቁንም ምናሴ፣ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት እንዲፈጽም ይሁዳን ካሳተበት ኀጢአት ሌላ፣ ኢየሩሳሌምን ከዳር እስከ ዳር እስኪሞላት ድረስ ብዙ ንጹሕ ደም አፈሰሰ።
ባሮች ብንሆንም፣ አምላካችን ግን ባሮች ሆነን እንድንቀር አልተወንም፤ ነገር ግን በፋርስ ነገሥታት ፊት ቸርነቱን አሳየን፤ የአምላካችንን ቤት እንደ ገና እንድንሠራና ፍርስራሾቿን እንድንጠግን አዲስ ሕይወት ሰጠን፤ በይሁዳና በኢየሩሳሌምም የመከላከያ ቅጥር ሰጠን።
ይሁዳን ፈጽመህ ጥለኸዋልን? ነፍስህስ ጽዮንን ተጸየፈቻትን? ፈውስ እስከማይገኝልን ድረስ፣ ለምን ክፉኛ መታኸን? ሰላምን ተስፋ አደረግን፤ ሆኖም በጎ ነገር አላገኘንም፤ የፈውስን ጊዜ ተጠባበቅን፤ ነገር ግን ሽብር ብቻ ሆነ።
ግራ እንደ ተጋባ ሰው፣ ለመታደግም ኀይል እንዳጣ ተዋጊ ትሆናለህ? እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ በመካከላችን አለህ፤ በስምህም ተጠርተናል፤ እባክህ አትተወን።
ምድሬን በድን በሆኑ አስጸያፊ ጣዖቶቻቸው ስላረከሱ፣ ርስቴንም በአሳፋሪ ነገሮች ስለ ሞሉ፣ ላደረጉት በደልና ኀጢአት ዕጥፍ እከፍላቸዋለሁ።”
እኔን ትተውኝ፣ ይህን ስፍራ የባዕድ አማልክት ቦታ አድርገውታልና። እነርሱም ሆኑ አባቶቻቸው፣ የይሁዳ ነገሥታትም ለማያውቋቸው አማልክት ሠውተዋል፤ ይህንም ስፍራ በንጹሓን ደም ሞልተውታል፤
ስለዚህ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ነቢያት እንዲህ ይላል፤ “ከኢየሩሳሌም ነቢያት፣ በምድሪቱ ሁሉ ርኩሰት ተሠራጭቷልና፤ መራራ ምግብ አበላቸዋለሁ፤ የተመረዘም ውሃ አጠጣቸዋለሁ።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በላይ ያሉትን ሰማያትን መለካት፣ በታችም ያሉትን የምድር መሠረቶች መመርመር ከተቻለ፣ በዚያ ጊዜ የእስራኤልን ዘር ሁሉ፣ ስላደረጉት ነገር ሁሉ እጥላቸዋለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር።
አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፤ አትፍራ፤ እኔ ከአንተ ጋራ ነኝና” ይላል እግዚአብሔር፤ “አንተን የበተንሁበትን ሕዝብ ሁሉ፣ ፈጽሜ ባጠፋም እንኳ፣ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም። ተገቢውን ቅጣት እሰጥሃለሁ እንጂ፣ ያለ ቅጣት አልተውህም።”
በእነዚያ ጊዜያት፣ በዚያ ዘመን፣” ይላል እግዚአብሔር፤ “የእስራኤል በደል ይፈለጋል፤ አንዳችም አይገኝም፤ የይሁዳም ኀጢአት ይፈለጋል፤ ከቶም የለም፤ እንዲተርፉ ያደረግኋቸውን ቅሬታዎች እምራለሁና።
የያዕቆብ ዕድል ፈንታ የሆነው ግን እንደ እነዚህ አይደለም፤ እርሱ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነውና፤ እስራኤልም የርስቱ ነገድ ነው። ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።
እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ ይህን አይተሃልን? የይሁዳ ቤት በዚህ ቦታ የሚፈጽሙት ጸያፍ ተግባር ቀላል ነገር ነውን? ምድሪቱንስ በዐመፅ በመሙላት ዘወትር ያስቈጡኝ ዘንድ ይገባልን? እነሆ፤ ቅርንጫፉን ወደ አፍንጫቸው አቅርበዋል!
እርሱም እንዲህ ሲል መለሰልኝ፤ “የእስራኤልና የይሁዳ ቤት ኀጢአት እጅግ በዝቷል፤ ምድሪቱ በደም ተጥለቅልቃለች፤ ከተማዪቱም ግፍን ተሞልታለች። እነርሱ፣ ‘እግዚአብሔር ምድሪቱን ትቷታል፤ እግዚአብሔር አያይም’ ይላሉ፤
“ይሁን እንጂ እስራኤላውያን ሊሰፈርና ሊቈጠር እንደማይችል እንደ ባሕር አሸዋ ይሆናሉ፤ ‘ሕዝቤ አይደላችሁም’ በተባሉበት ቦታ፣ ‘የሕያው አምላክ ልጆች’ ተብለው ይጠራሉ።
አለዚያ ገፍፌ ዕርቃኗን አስቀራታለሁ፤ እንደ ተወለደችበትም ቀን አደርጋታለሁ፤ እንደ ምድረ በዳ፣ እንደ ደረቅም ምድር አደርጋታለሁ፤ በውሃ ጥምም እገድላታለሁ።
እናንተ የእስራኤል ልጆች፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እግዚአብሔር በምድሪቱ በምትኖሩት ላይ የሚያቀርበው ክስ አለውና፤ ምክንያቱም ታማኝነት የለም፤ ፍቅርም የለም፤ እግዚአብሔርንም ማወቅ በምድሪቱ የለም።
የርስቱን ትሩፍ ኀጢአት ይቅር የሚል፣ የሚምር እንደ አንተ ያለ አምላክ ማነው? ለዘላለም አትቈጣም፤ ነገር ግን ምሕረት በማድረግ ደስ ይልሃል።
“በዚያ ቀን የይሁዳን መሪዎች በዕንጨት ክምር ውስጥ እንዳለ የእሳት ምድጃ፣ በነዶም መካከል እንዳለ የፋና ነበልባል አደርጋቸዋለሁ፤ በግራና በቀኝ ዙሪያውን ያሉትን ሕዝቦች ይበላሉ፤ ኢየሩሳሌም ግን ከስፍራዋ ንቅንቅ አትልም።
ከመካከላቸው እጅግ ደካማ የሆነው እንደ ዳዊት፣ የዳዊት ቤትም ፊት ፊታቸው እንደሚሄድ እንደ እግዚአብሔር መልአክ፣ እንደ አምላክ ይሆንላቸው ዘንድ በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን እግዚአብሔር ይከልላቸዋል።