ኤርምያስ 51:27 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በምድር ሁሉ ላይ ሰንደቅ ዐላማ አንሡ! በሕዝቦች መካከል መለከትን ንፉ! ሕዝቦችን ለጦርነት በርሷ ላይ አዘጋጁ፤ የአራራትን፣ የሚኒንና የአስከናዝን መንግሥታት፣ ጠርታችሁ በርሷ ሰብስቧቸው፤ የጦር አዝማች ሹሙባት፤ ፈረሶችንም እንደ አንበጣ መንጋ ስደዱባት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድር ላይ ዓላማን አንሡ በአሕዛብም መካከል መለከት ንፉ፥ አሕዛብንም ለጦርነት በእርሷ ላይ አዘጋጁ፤ የአራራትንና የሚኒን የአስከናዝንም መንግሥታት ጥሩባት አለቃንም በእርሷ ላይ ሹሙ፤ እንደ ጠጉራም ኩብኩባ ፈረሶችን በእርሷ ላይ አውጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አደጋ ለመጣል የሚያስችል ምልክት ስጡ! ሕዝቦች ሁሉ መስማት እንዲችሉ እምቢልታ ንፉ! ባቢሎንን ይወጉ ዘንድ ሕዝቦችን አዘጋጁ! የአራራት፥ የሚኒና የአሽኬናዝ መንግሥታት አደጋ እንዲጥሉ ንገሩአቸው፤ የጦር አዛዥ የሚሆን ሰው ሹሙ፤ ብዛታቸው እንደ አንበጣ መንጋ የሆነ ፈረሶችን አምጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በምድር ላይ ዓላማን አንሡ፤ በአሕዛብም መካከል መለከትን ንፉ፤ አሕዛብንም ለዩባት፤ የአራራትንና የሚኒን የአስከናዝንም መንግሥታት እዘዙባት፤ ጦረኞችንም በላይዋ አቁሙ፤ ብዛታቸው እንደ አንበጣ የሆኑ ፈረሶችን በላይዋ አውጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድር ላይ ዓላማን አንሡ በአሕዛብም መካከል መለከት ንፉ፥ አሕዛብንም አዘጋጁባት፥ የአራራትንና የሚኒን የአስከናዝንም መንግሥታት ሰብስቡባት አለቃንም በላይዋ አቁሙ፥ እንደ ጠጕራም ኩብኩባ ፈረሶችን በላይዋ አውጡ። |
ናሳራክ በተባለው አምላኩ ቤተ ጣዖት ገብቶ በመስገድ ላይ ሳለ፣ አድራሜሌክና ሳራሳር የተባሉ ልጆቹ በሰይፍ ገደሉት፤ ከዚያም አምልጠው ወደ አራራት ሸሹ። ልጁ አስራዶንም በምትኩ ነገሠ።
ናሳራክ በተባለው አምላኩ ቤተ ጣዖት ገብቶ በመስገድ ላይ ሳለ፣ አድራሜሌክና ሳራሳር የተባሉ ልጆቹ በሰይፍ ገደሉት፤ ከዚያም አምልጠው ወደ አራራት ሸሹ። ልጁ አስራዶንም በምትኩ ነገሠ።
“በሕዝቦች መካከል ተናገሩ፤ አስታውቁም፤ ሰንደቅ ዐላማ አንሡ፤ ዐውጁ፤ አንዳች ሳታስቀሩ፣ እንዲህ በሉ፤ ‘ባቢሎን ትያዛለች፤ ቤል ይዋረዳል፤ ሜሮዳክ በሽብር ይሞላል፤ ጣዖቶቿ ይዋረዳሉ፤ አማልክቷም ይሸበራሉ።’
የታላላቅ መንግሥታትን ማኅበር፣ ከሰሜን በባቢሎን ላይ አስነሣለሁ፤ እነርሱም በርሷ ላይ ይሰለፋሉ፤ መጥተውም ይይዟታል። ቀስቶቻቸው ባዶ እጃቸውን እንደማይመለሱ፣ እንደ ሥልጡን ተዋጊዎች ናቸው።
በባቢሎን ቅጥር ላይ ዐላማ አንሡ ጥበቃውን አጠናክሩ፤ ዘብ ጠባቂዎችን አቁሙ፤ ደፈጣ ተዋጊዎችን አዘጋጁ እግዚአብሔር በባቢሎን ሕዝብ ላይ የወሰነውን፣ ዐላማውን ያከናውናል።
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል በራሱ ምሏል፤ እንደ አንበጣ መንጋ በሆነ ብዙ ሰው አጥለቀልቅሻለሁ፤ እነርሱም በድል አድራጊነት በላይሽ ያቅራራሉ።
“እናንተ የብንያም ልጆች፤ ክፉ ነገር፣ ታላቅም ጥፋት ከሰሜን ድንገት ይመጣልና፣ ከኢየሩሳሌም ሸሽታችሁ አምልጡ፤ በቴቁሔ መለከትን ንፉ፤ በቤትሐካሪም ላይ ምልክት ከፍ አድርጋችሁ አሳዩ።
ኢየሩሳሌምን እንዲወጉ አሕዛብን ሁሉ እሰበስባለሁ፤ ከተማዪቱ ትያዛለች፤ ቤቶች ይበዘበዛሉ፤ ሴቶችም ይደፈራሉ፤ የከተማዪቱ እኩሌታ ይማረካል፤ የሚቀረው ሕዝብ ግን ከከተማዪቱ አይወሰድም።
ከብቶቻቸውንና ድንኳኖቻቸውን ይዘው ሲመጡ ልክ የአንበጣ መንጋ ይመስሉ ነበር፤ ሰዎቹንም ሆነ ግመሎቻቸውን ለመቍጠር አዳጋች ሲሆን፣ የሚመጡትም ምድሪቱን ለማጥፋት ነበር።